"ሠራተኛው በአሁኑ ሰዓት የመኖር ያለመኖር ጥያቄ ውስጥ ገብቷል" ኢሠማኮ
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) ጠቅላላ ጉባኤ፤ በኢትዮጵያ የሠላም ሁኔታ እና በሠራተኛ ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአቋም መግለጫ መላኩን አስታውቋል።
ጉባኤው በአንዳንድ ክልሎችና አካባቢዎች ባለማቋረጥ በተከሰቱ የእርስ በእርስ ግጭቶች የተነሳ፤ ሠራተኛው በሕይወት የመኖር መብት ጥሰት፣ በድርጅቱ መዘጋትና ውድመት ዙሪያ ያለውን ሁኔታ መመርመሩን ገልጿል።
"በዚህና በሌሎች ምክንያቶች በየዕለቱ እያሻቀበ ያለውን የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ቀውስ ዝቅተኛ ምንዳ ተከፋይ ሠራተኛና ቤተሰቦቹ ፈፅሞ ሊቋቋሙት ከማይችሉ ደረጃ መድረሳቸውን ከሕይወት ተሞክሮ ማጤን ተችሏል" ሲልም ገልጿል።