የኤርትራና የትህነግ ጉዳይ ግራ ላጋባችሁ!
በትህነግና ኤርትራ ጉዳይ ላይ አልፎ አልፎ የሚነገሩ ጉዳዮች አሉ። ብዙዎቹ በቁማሮች መክሸፍ የተጀመሩ፣ በቁማርነትም የቀጠሉ ናቸው። ግራ የገባችሁ ካላችሁ አንዳንዶቹን እንሆ!
1) የደቡብ አፍሪካው ስምምነት ለትህነግ ምቹ አልነበረም። ትጥቅ በወር ውስጥ እንዲፈታ የሚያዘውን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮች ነበሩት። ይሁንና ከደቡብ አፍሪካ ፈራሚዎች ውጭ ብርሃኑ ጁላና ታደሰ ወረደ ዋና ተዋናይ ሆነው የወጡበት የናይሮቢ ስብሰባ ሌላ የጓዳ እርቅ ይዞ መጣ። የደቡብ አፍሪካውን ስምምነት ወደ ጎን ትተው ትህነግን አትርፈው በቀጣይ ስለሚሰሩት በዋነኛነት ኤርትራንና አማራን ስለመምታት ትኩረት አደረጉ።
2) በናይሮቢው የጓዳ ስምምነት መሰረት የአማራን ልዩ ኃይል ቀጥሎም ፋኖን ትጥቅ በማስፈታት የአማራን ግዛቶች ለትህነግ አሳልፎ መስጠት ላይ ገቡበት። በዚህ ወቅት ዋና አማካሪዎቹ የትህነግ ጀኔራሎች ነበሩ። ቀጣይ ኤርትራ ነው ተባለ። በዚህ መሰረት አብይ ለሚኒስትሮቹ "ወጭ ቀንሱ ከህወሓት ጋር ከነበረው የባሰ ቀጠናዊ ጦርነት አለብን" ብሎ ትዕዛዝ እስከመስጠት ደርሷል። ቀስ እየተባለ አሰብን ስለመያዝ አጀንዳ ሆነ። አጫፋሪዎቹ ደግሞ የትህነግ ደጋፊዎች ነበሩ።
3) አብይ አህመድና ትህነግ ኤርትራን ስለማጥቃት አጀንዳ አድርገው የመከላከያ ጀኔራሎቹ ጋር ቤተ መንግስት ውስጥ ክርክር ጭምር ተደርጎበታል። የትህነግ ጀኔራሎች ስለ ኤርትራ ግምገማ ሲያደርጉ በዋነኛነት "የኤርትራ ወጣት ተሰድዶ አልቋል። ኤርትራ ወጣት የለውም። እኛ ብዙ የሰው ኃይል አለን። ሻቢያን እናውቀዋለን። እንመታዋለን" ብለዋል። ያው በሰው ማዕበል መሆኑ ነው። አብይ አህመድም የትህነግን ታጣቂ ትጥቅ ያላስፈታው ለዚህ አላማ ጭምር ነው። "እናንተ በእግረኛ፣ እኔ በከባድ መሳሪያና ድሮን ተቀናጅተን" ተባብለው መክረዋል። ለኤርትራ ቀናኢነት አላቸው የተባሉ የመከላከያ ጀኔራሎች በትህነግ ጀኔራሎች ተተክተው ጦርነቱን የሚመሩበት መንገድ ሁሉ ተወርቶበታል።
አብይ አሰብን እይዛለሁ ብሎ ከሁለት የአውሮፓ አገራት ቀጥተኛ ድጋፍ ማግኘቱን ተናግሯል። አሜሪካም ትህነግና አብይ ከተስማሙ ኢሳያስን ማስወገድን እንደምትፈልግ አስበዋል። በዚህ መሃል ግን ችግሮች ተፈጠሩ። ፋኖን በሶስት ቀን ትጥቅ አስፈትቸ የአማራን ርስት አሳልፌ እሰጣችኋለሁ ያለው አብይ ችግር ገጠመው። ጦርነቱ እንዳሰበው ሳይሄድ ቀረ።
4) ኤርትራን ስለመምታት ሲታሰብ ትህነግ ያሰበው "ኤርትራ ከተመታች ሌላው እዳው ገብስ ነው" የሚል ጭምር ነው። ለምሳሌ ኤርትራ ሳትመታ አማራ ጋር ብገጥም ኤርትራም ስለምታግዝ መጀመሪያ ከአብይ ጋር ሆኘ እመታታለሁ የሚል እሳቤ ነው። ከሶስተኛው የትህነግ ወረራ በፊት ወደ አዲስ አበባ ከመዝመታችን በፊት አስመራን እንምታ የሚሉ ነበሩ። አሰብን ይዘን ከበባውን እንስበር የሚል ክርክርም ነበር። ተሸንፈው ሲመለሱም "ኤርትራን ብንመታ ኖሮ" የሚሉት ሌላ ጊዜ አግኝተዋል።
አማራው የቆመው በኤርትራ ድጋፍ ስለሆነ ቀጥለን በይፋ ወደ አማራ እንዘምታለን የሚል የተሳሳተና የንቀት ግምገማቸውም ለውሳኔነት ውሏል። ከዚህ ባሻገር አሰብን ከያዝን በኋላም ቢሆን ምናደርገውን እናደርጋለን ብለው ከአብይ ጋርም ሌላ ቁማር ጀምረው ነበር። ኤርትራን ከአብይ ጋር ሆኖ መውጋት ግን በሙሉ ድጋፍ ያለፈ አይደለም። የአማራ ክልሉ ጦርነትና ግዛት አሳልፎ መስጠት ጉዳይ ቃል በተገባላቸው መሰረት ባለመሄዱ "አብይ የራሱን የቤት ስራ ሳይሰራ እኛን መጠቀሚያ ሊያደርግ ነው" የሚል ስጋትም እንደነበር ተሰምቷል። ከዚህ ባሻገር የኤርትራ ተቃዋሚዎች ከኢሳያስ ጋር ያብራሉ፣ ከአዲሱ የኤርትራ ትውልድ ጋር እንቀያየማለን የሚሉ ጥቂት ሰዎች አልጠፉም።
5) ታዲያ ኢሳያስ ምኑ ሞኝ ነው? አብይ የትህነግን ግሪሳ አፈስበታለሁ ብሎ ሲያስብ ፣ ወደ አሰብና አስመራ ፊቱን ያዞራል የተባለውን የትህነግ ኃይል "ወደ አዲስ አበባም መዞር ይችላልኮ!" የሚል ሀሳብ ብቅ አለ። በአጭሩ ኢሳያስ የትህነግ ሰዎችን "ግሪሳውን" ወደ አዲስ አበባ አዙሩት አላቸው። የትህነግ ሰዎች አብይ በተናገረው ፍጥነት አልፈፀመም ያሉትን ሁሉ አዲስ አበባን ይዘንም ሆነ ሳንይዝ እንፈፅመዋለን የሚል አማራጭ ያዙ። አብይ ከኢሳያስ ጋር ከሚያብሩብኝ ብሎ የበለጠ እንዲሰራላቸውም ይፈልጉ ነበር። በዚህ ወቅት ትህነግ በመደበኛውም በጥቁር ገበያም ዋጋዋ ከፍ ያለ መሰላት።
6) ትህነግ ኤርትራ ጋር ግንኙነት ሲጀምር ቢያንስ በአማራ ጉዳይ ገለልተኛ እንዲሆን የሚል ነው። ከዛም አብይ ፈጥኖ አልፈፀመልንም የሚሉትን የግዛት ወረራ ፈፅመው መደራደሪያ ከፍ ማድረግ ነበር። በዱባዩ የኤርትራና የትህነግ ውይይት ቁርጡ ተነገራቸው። "እንዲህ አይነት አካሄድ አይጠቅምም" ተባሉ። "የፈለጋችሁት ስልታዊ እንጅ ስትራቴጅካዊ ወዳጅነት አይደለም። የምር ሰላም ከፈለጋችሁ ከአማራ ጋር ተነጋገሩ" ተባሉ። ትህነግ ባያምንበትም ለይምሰል በሚዲያም ከሚዲያ አለፍ ካለም በምናምናቸው ሰዎች በኩል ከአማራ ጋር እየተነጋገር እንደሆነ እናሳያቸው አለ። ይህ በተነገራቸው ማግስት የትህነግ ሚዲያዎች ስለ አማራና ትግራይ ህዝብ ሰላምና ውይይት በተደጋጋሚ አወሩ። በጦርነቱ ወቅት ከትህነግ ጎን የነበሩ ትህነግ የአማራ ተወካይ ያደረጋቸው ስለ ሁለቱ ህዝብ ውይይት ፃፉ። ተናገሩ። ከዚህ ያለፈ ግን ብዙ አልተሄደበትም።
7) ኢሳያስ አብይ የትህነግን ግሪሳ ከሚያዘምትብኝ እኔ አዘምትበታለሁ ብሎ ከትህነግ ሰዎች ጋር ሲነጋገር ትህነግን ለሁለት ከፈለው። ኤርትራን እንውረር ያሉት እነ ፃድቃን ጎን በ1993 ከትህነግ የተባረሩት የድሮዎቹ አመራሮች ጭምር ተቀላቀሉ። የእነ ደብረፅዮን ትህነግ ለአብይ ሽምግልና ልኮ ወጥቶ ወርዶ ስልጣን ሲነሳው አማራ ላይ የታወጀው በፈለጉት መልኩ አልሄድ ሲል ኤርትራ ትሻለናለች አለ።
8/ኤርትራን የመረጠው ትህነግ ግን ሌላ ተስፋ ጨምሮ ነው። ባለፈው ኤርትራ ወጣት የላትም ብሎ ያቀረበ ቡድን አሁን ደግሞ "ትንሽ ከታገስን ኢሳያስ አርጅቷል። ይሞታል። ወጣቱ ጋር መግባባትም የበላይነት መውሰድም እንችላለን" ብሎ አስቦ ነው። ብዙ በተስፋ የሚያወሩት አለ።
9) አብይ አህመድ ኬንያ ላይ በብርሃኑ ጁላ በኩል፣ ሀላላ ኬላና አዲስ አበባ ራሱ በነገራቸው መሰረት የአማራ ክልል ጦርነትን ማስኬድ ሲያቅተው ደግሞ ትህነግ ሌላ አማራጮችን አስበው ነበር። የትህነግ ዩቱዩበሮች ፋኖን ደገፍን ያሉት መጨረሻ ላይ በትግሉ ነበርን ለማለት ጭምር ነው። ሌሎች ጉዳዮችም አሉ።
ቁማሩ ነገም ከነገ ወዲያም ይቀጥላል። አብይ አህመድ አማራውን መትቶ ቃል የገባላቸውን ቢፈፅም ወደ ኤርትራም አብረው መዞራቸው አይቀርም ነበር። ነገም ትንሽ ክስተት አሰላለፉን ሁሉ ትቀይራለች።
ቁማሮቹ የተሳሳቱ ቁማሮች፣ የጓዳ ስምምነት ውጤቶች ናቸው። አንተ እዘምትበታለሁ ስትል አፈሙዙ በአፍታ ወደአንተ ይዞራል። ሌላ ትጀምራለህ! የቁማር አዙሪት ነው!