የዋዛ ደብዳቤ የሚመስለው የዋህ ሞልቷል! ፋኖ ያቆሰላት የጓዳ ስምምነቷ ጣር ነች!
" ከእስካሁኑ በተለየ ሁኔታ" ትላለች ጣረሞቷ!
ከሰላም ስምምነቱ ባሻገር የኦሮሞ ብልፅግና እና ትህነግ ኬንያ ላይ እፍ ክንፍ ብለው ያወሩባት፣ ሀላላ ኬላ፣ ናዝሬት፣ አዲስ አበባ ወዘተ የመከሩባት የጓዳ ስምምነት ታምማ እያጣጣረች ነው። ዛሬ እሪታዋ ተሰምቷል። የጓዳ ስምምነት ዋና አንጓዋ "አንድ ላይ ሆነን አማራና ኤርትራን እንምታ" የምትል ነበረች። ብልፅግና አማራውን መትቶ በአስቸኳይ ከትህነግ ጋር ኤርትራን መምታት ነበር ውሉ። ብልፅግና በቀናት ውስጥ እጨርሰዋለሁ ያለው አማራ ላይ የተከፈተ ዘመቻ እንዳሰበው ሳይሆን ቀረ። የአማራው ትግል የጓዳ ስምምነቷን ጊዜ በላው። ክፉኛ አቆሰላት። ጭራሽ ትህነግን ሌላ አማራጭ ውስጥ አስገባው። "ሞኝ አይደለሁም በሌላው በኩልም ላታልል" ብሎ እንዲወላውል አደረገው። መአት መወላወል፣ መአት ማደናገር ውስጥ ገባ።
ይች ደብዳቤ ሌላ የጓዳ ስምምነቶን መመንመን የምታሳይ ናት። ዝም ብላ ብጣሽ ትዕዛዝ አይደለችም። መአት የያዘች የጣር ደብዳቤ ነች።
ይሄውላችሁ!
ትህነግ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ከብትና ወርቅ ላይ ትኩረት አደረገ። ከአጎራባች አካባቢዎች ከብት መዝረፍ ጀመረ። ከአፋር ጋር የከረመው ግጭት መነሻ ይህ ነው። በዋልድባ በአንድ ክስተት ብቻ ህዝቡን ፈጅተው ከአምስት መቶ በላይ ከብት ዘርፈው ነው የሄዱት። በዋግኸምራና ራያ ተመሳሳይ ነው። ከዚህ ባለፈው በገበያም በርካታ ከብቶች ወደ ትግራይ ይሄዳሉ። ለእርሻ ወዘተ አይደለም። ለስንቅ ነው። አስቃጥላ ወይንም የወታደር የቆርቆሮ ስጋ ሲታሸግ ነው የከረመው። ይህን ጉዳይ ከወራት በፊቶ በአንድ ፅሁፌ ጠቅሸው የተወሰኑ የትህነግ አክቲቪስቶች ተንዘርዝረዋል። በሌላ ጉዳይ አስመስለው ስሜን አንስተዋል። ለምን እንደተበሳጩ አውቄያለሁ።
የሆነ ሆኖ ያ በጦርነቱ ወቅት ወደ ትግራይ በአውሮፕላን መሳሪያ ሲያልፍ "በአየር ክልላችን አኛ ሳንፈቅድ ወፍ አይበርም" ሲል የነበረ የብልፅግና ኃይል የአማራን ንፁሃን በድሮን ሲጨፈጭፍ ትግራይ ውስጥ ትጥቅ አስፈታዋለሁ እያለ ለአማራና ኤርትራ በሚል ያስቀመጠው ኃይል የወታደር ቀለብ ሲሰበስብ ደርሶበት ይችን ደብዳቤ በትዕዛዝ አስፅፏል። ልዩ ኃይሉን ትጥቅ እንዲያወርድ፣ መከላከያን ገብተህ ጨርስ ብሎ ደብዳቤ የፃፈው ብአዴን አሁን ደግሞ ለትህነግ ስንቅ እየተሰራ መሆኑን ዘግይቶ ከትግራይ ወዳጆቹ በሰማው አብይና ብርሃኑ ጁላ ትዕዛዝ ይችን ደብዳቤ ፅፏል።
ትህነግ በበርካታ የፕሮፖጋንዳ ዳመና ውስጥ ሌላ ጉዳይ እየሰራ ነው የከረመው። በበርካታ የይምሰል አጀንዳ እያጫወተ ሌላ ጉዳይ ላይ ነው የከረመው። ይሄው በእነ አብይ ትዕዛዝ የወጣው ደብዳቤ ማሳያ ነው።
1) የትህነግ የፓርቲ እውቅና እና ጠቅላላ ጉባኤ ስም ብዙውን ሲያወናብደው ከርሟል። በቀጥታ እውቅና ስጡኝ ብሎ ወደ ምርጫ ቦርድ ሲልኩት አላቅማማው ተደብቆም ቢሆን ሄደ። በደጋፊዎቹ ሲነቃበት ደግሞ ጠቅላላ ጉባኤ ገባ። ብልፅግናም ሆነ ሌላ ኃይል እንዳያደናቅፈው "እንነጋገርበታለን" ወዘተ እያለ ሲያስፈልግ አዲስ አበባ መጥቶ እየለመነ ከረመ። ይች ግን ሽፋን ነች። ዋናው ዝግጅት ሌላ ነው። ያደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በቦርድ እውቅና እንደማያገኝ ያውቃል። ለወዳጅም ለጠላቱም ጅል መስሎ የከረመው በሌላ አማራጭ ላይ ስለቆመ ነው።
2) የሰላም ስምምነቱን ሲፈልግ ተዋዋይ፤ ሲፈልግ ደጋፊዎቹን፣ ሲፈልግ የእሱን ፈራሚዎች በሚያወዛግብ መካከል ልዩነት ያለ አስመስል አጀንዳ አደረገው። ልዩነቱ በሰላም ስምምነቱ ብቻ አይደለም። የሰላም ስምምነቱ ላይ መአት ማደናገሪያ አምጥቶ ብዙዎቹን በዚህ ዙሪያ አከረማቸው። አንዴ አከብረዋለሁ፣ አንዴ አላከብረውም፣ አንዴ ፈረምኩ ሌላ ጊዜ አልፈረምኩም ሲል የከረመው ራሱን ስምምነቱን መጫዎቻ አድርጎት ነው። ብዙዎችን በዚህ ዙሪያ እያጫወተ ዋናውን ጉዳይ ሌላ አድርጓል።
3) ሌላኛው ማደናገሪያ ፋኖ ጋር ያለው ጉዳይ ነው። በአንድ በኩል ከብልፅግና ጋር የተዋዋለው አለ። በሌላ በኩል የተወሰኑ የሚዲያ ሰዎቹን የፋኖ ትግል ደጋፊ አስመስሏል። በቀናት ውስጥ ብልፅግና አጠናቀዋለሁ ያለው ትግል እንዳልሆነ ሲያውቅ ተጠባባቂ አድርጎታል። ግን የደከመ፣ አመራሩ የተበታተነ እንጅ ጠንካራ የአማራ ትግልን አይፈልግም። አማራ በወርድና በልኩ የሚወከልበት ትግል ትህነግን አናሳ ያደርገዋል። አይፈልገውም። ስለሆነም በሶስት መስመር ተሰማራ። መሬት ላይ ያለው የፋኖ ዕዝ ላይ በሁሉም አብረን እንስራ ሽማግሌ ልኳል። ብልፅግና ጋር ተዋውሏል። ብልፅግናን ይመክራል። አማራው ድቅቅ ውድም እንዲል ይፈልጋል። በብልፅግና የደቀቀ ቢቻል "ህወሓት ማረኝ" የሚል አማራ ቢፈጠር ደስታው ነው። ስለዚህ በመካሪዎቹ በኩል "አይዞህ መትተኸዋል" ይላል። ጀኔራሎቹም ሆነ ፖለቲኸኞቹ አራት ኪሎና ጦር ኃይሎች ሲመጡ አብይና ብርሃኑ ጁላን መክረው የቻለትን ያግዛሉ። በብልፅግና አመራሩ ተመትቶ የደከመ፣ ትህነግን መንገድ እየመራ "እንኳን ትግላችን ከመሞት ዳነ፣ ባለውለታችን ናችሁ" ብሎ የሰጡትን የሚቀበል አማራ ይፈልጋል። በሌላ በኩል ደግሞ ውጭ የተቀመጡ የፋኖ ወኪል ነን ያሉት አካላትን "በዚህ ፋኖ አታሸንፉም" ብሎ ይመክራል። የአሁኑን ፋኖ የተበታተነ አመራር ያለው፣ ለአመራር የማይታዘዝ ስለሆነ እስከዛው በስሙ እየተጠጠቀሙ ሌላ እንዲያሰለጥኑ ጭምር ሰነድ ሰጥቷል። እስካሁን የረባ አልተሳካለትም። ግን በሁሉም ያደናግራል። ያጫውታል።
4) ሁሉንም ማደናገሪያ ተጠቅም ራሱን ማጠናከር ነው። አንደኛው እኔ ስበረታ መደራደሪያው በእጀ ይሆናል ነው። ለዚህም ለውጮቹ የሰላም ስምምነቱ ፈረሰ ብሎ፣ ለትግራይ ህዝብ ሰራዊቴን ሊያፈርሱት ነው ብሎ፣ ለአማራው ትግልህን እደግፋለሁ ብሎ፣ ለኤርትራና ሶማሊያ ሉአላዊነታችሁን አከብራለሁ ብሎ እየሰራ ነው። የመጀመሪያ በጋራ ትግል ስም የአማራን ግዛቶች በእጁ ማስገባት ነው። "አዲስ አበባ እንገባለን" ብሎ መንገድ ላይ ከቀናው የሚዘውን ይይዛል። አማራው ተዳክሞ መንገድ መሪ ብቻ ይሆነኛል ብሎ ካሰበ ይቀጥላል። ካልሆነ የያዘውን ይዞ ይመለሳል። አማራን ተጠናክሮ በራሱ ቀዳሚነት ወደ አራት ኪሎ ካመራ ትህነግ ከሰረ ነው። ፊት አውራሪነቱን ይነጠቃል። በወርድ መለካት ይመጣል። ይህን ደግሞ በግልፅ አንቀበልም ብለው አቋም ይዘውበታል። "እኩልነት እኛን አናሳ ያደርገናል" ብለው የወሰኑት ጉዳይ ነው።
የሰሞኑ "የትግራይ ቤተ ክርስትያን" አዋጅ አንዱ ማሳያ ነው። የትህነግ አብሪ ነው። በውትድርናው አብሪ ማለት ከዋናው ኃይል በፊት ቀድሞ ደርሶ መረጃ የሚሰበስብ፣ መንገድ መሪ ማለት ነው። "መንበረ ሰላማ"ም የትህነግ መሪ ነው። ወዲያ ወዲህ አይቶ የሚያመች የሚመስለውን ለመያዝ ሲል የጓዳ ውሏ እየለየላት ይመስላል።
ዋናው ቁም ነገር ግን ይች ደብዳቤ የጓዳ ስምምነቱ ጣረሞት ማሳያ ነች። የጓዳ ስምምነቱን ደግሞ የመታው የአማራው ትግል ነው።የፋኖ ትግል ከመስመሩ ሊወጣ ሲል የምንመክረውን ያህል፣ ከአማራው እሴትና ጥቅም የሚጋጩ ጉዳዮች እንዳይከሰቱ የምንወቅሰውን ያህል የሁለቱን ክፉዎች የጓዳ ውል መትቶ እንዲህ ስላስጮኻት "አበጀህ" እንለዋለን!
አማራን በአንድ ሰሞን መትተው ውሏን እንደሚፈፅሟት ቃል የገቡት አብይ አህመድ፣ ብርሃኑ ጁላ፣ ሬድዋን ሁሴን ደግሞ ሲጨንቃቸው በትዕዛዝ ደብዳቤ መፃፍ በማይሰለቸው ብአዴን በኩል ይችን አስወጥተዋል። የዋዛ ጉዳይ የሚመስለው የዋህ ምልቷል።