ለተከበራችሁ የሕብረት ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በቁጥር ኢካገባ/619/14 ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. በፃፈው ደብዳቤ መሰረት የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) ስራ ስለጀመረ የባንካችንን ባለአክስዮኖች መረጃ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ በመተካት ለመመዝገብ እንዲቻል መረጃውን እስከ ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሞልተን እንድንልክ ተጠይቋል፡፡
ስለሆነም የፋይዳ ቁጥርዎን (FAN/FCN) ፣ የአድራሻ ለውጥ አድርገው ከሆነ አዲሱን አድራሻ፣ ኢሜይል፣ ስልክ ቁጥር፣ የቤት ቁጥር፣ ሀገር፣ ክልል፣ ከተማ፣ ክ/ከተማ፣ ወረዳ፣ ቀበሌ፣ ባለአክሲዮኑ ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የድርጅቱ ወኪል ሙሉ መረጃ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በኢሜል አድራሻ ShareAdminstration@hibretbank.com.et እንድትልኩና መላካችሁን በስልክ ቁጥር 011-4-70-49-32 እንድታሳውቁን ፣ በዋና መ/ቤት የአክሲዮን አስተዳደር ክፍል በመቅረብ ወይም በሚቀርባችሁ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ እንድታስመዘግቡ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!