በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽ/ቤቶች መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል የጋራ ዕቅድ ተዘጋጀ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከአለም ባንክ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በግጭት ምክንያት ለተጎዱ አምስት ክልሎች የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎችን መልሶ ለማደራጀት የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዐቶችን ገዝቶ ድጋፍ ለማድረግ ከትግራይ፣ ቤኒሻንጉል፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የክልሉ የበላይ ኃላፊዎች፣ ም/ኃላፊዎች ፣ የሲቪል ምዝገባ ዳይሬክተር፣ የእቅድና በጀት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር እና አጋር አካላት በተገኙበት በጋራ የትግበራ ዝርዝር እቅድ መዘጋጀቱ ተገልፆል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋየ ወልዴ እንደተናገሩት የመድረኩ ዓላማ በግጭት ምክንያት ለተጎዱ 5ቱ ክልሎች መልሶ ለማደራጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን መለየት እና በምዝገባ ወቅት ያለባቸውን ቁልፍ ችግር በመለየት ከክልሎች ጋር በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት መወያየት ነው ብለዋል።
አክለውም በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው አምስቱ ክልሎች በሚደረግላቸው የግብዓት እርዳታ ምዝገባውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
በመድረኩ ክልሎች የደረሰባቸውን የጉዳት መጠን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን መልሶ ለማቋቋም የሚያስፈልጋቸውን ግብአቶች በጋራ አቅደዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/