የማንበብ ልምዳችንን እናዳብር!!
———
ብዙዎቻችን አጫጭር የማህበራዊ ሚዲያ ፅሁፎችን ከማንበብ የዘለለ በትግስት የምንጠቀምበትን ረዘም ያለ ፅሁፍ የማንበብ ልምድ የለንም። ምንም እንኳ ሰው ከጉድለት ባይፀዳም በአባባል ደረጃ "ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል" ይባላል፣ ይህ የማንበብን ደረጃ ለመግለፅ የተፈለገበት አባባል ነው። የሱንና ፅሁፎችን በዐረቢኛም ሆነ በሌሎች በምንረዳቸው ቋንቋዎች ማንበብ መልመድ ትልቅ ተሰጦዖ ነው። ጊዜያችን በአጋጉል ነገርና በማይረባ ነገር ስልክ እየጎረጎሩ ማቃጠል አላህ ፊት ከተጠያቂነት አያድንምና በሚጠቅሙ ት/ት ነክ በሆኑ የሱንና ፅሁፎችና መፅሃፎችን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በትግስት አንብቦ ሀሳባቸውን ለመረዳት መሞከር ለላቀ አስተሳሰብና ሸሪዓዊ ነጥቦችን በማስረጃ ለማወቅ ይረዳል።
ታላቁ ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) اقرأ አንብብ ተብለዋል። ኢስላም የተስፋፋው በፅሁፍ ነው፣ ደጋግ ቀደምቶቻችን እነ ኢማሙ አሕመድ፣ ማሊክ፣ ሻፊዒይ፣ ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ትርሚዚይ፣ እነ ኢብኑ ተይሚየህ… (ሁሉንም አላህ ይዘንላቸውና) የመሳሰሉት ሊቃውንቶች ዲኑን ያስተላለፉልን በፅሁፍ ነው። ማንበብ ካልቻልንና ለማንበብ ትግስት ከሌለን እንዴት ይህን ዲን በሚገባ ልንረዳ እንችላለን?!
በዚህን ጊዜ ሁሉም ነገር ተመቻችቷል፣ ዐረቢኛ የሚችል የተለያዩ የኢስላም ልሂቃን ሳይደክማቸው የተለያዩ ኪታቦችን ፅፈውልን ሄደዋል፣ ዐረቢኛ የማይችል በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የሱንና መፅሃፎችን ማንበብ ይችላል። እነሱ ሲፅፉት ያልደከሙት እኛ ለማንበብ ደክመናል። በየ ደረጃው ለማንበብ ጥረት ማድረግ ግድ ይላል።
ስናነብ በማያሰላቸንና በሂደት ልምድ በምናደርገው መልኩ በትንሽ ትንሹ ሀሳቡን በደንብ እየተረዳን በማንበብ በሂደት ከፍ እያልን መሄድ እንችላለን።
🔸በዛው ልክ አጥፊ ከሆኑ ከጥመት ቡድኖችና ምንጫቸው ከማይታወቁ ልበ ወለድ የሆኑ የፈላሲፋ ፅሁፎችን ከማንበብ መጠንቀቅ ነው!! እንዲህ አይነት መፅሃፎችን ማንበብ የሚፈቀደው ለአንድ ነገር ብቻ ነው፣ እሱም ጠንካራ ሸሪዓዊ እውቀት ኖሮት ምላሽ (ረድ) መፃፍ ለሚፈልግ አካል ብቻ ነው።
"አንብብ" ተብለው የተላኩት የታላቁ ነቢይ ትውልድ (ኡማ) እንዴት አያነብም?!
የማንበብ ልምዳችንን እናዳብር!!
✍🏻ኢብን ሽፋ #join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa