👉 በቀብር ላይ ጠዋፍ
ጠዋፍ ማለት መዞር ማለት ሲሆን በተለያየ መልኩ ሊከሰት ይችላል ። በአንድ ነገር ዙሪያ መሄድ ጠዋፍ ይባላል ። ሀገር ለሀገርም መሄድ ጠዋፍ ይባላል ይህ ቋንቋዊ ትርጓሜው ሲሆን በሸሪዓ የሚፈለግበት ካዕባን በመዞር አላህን መገዛትን ነው ። አላህ ይህን አስመልክቶ ባሮቹን ዚያዝ እንዲህ ይላል : –
" وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ "
الحج ( 29 )
{ በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ } ፡፡
ጠዋፍ እንደየአድራጊው ንያ ብይኑ ይለያያል ። – አላህን የሚገዙበት ዒባዳ ይሆናል ።
– ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ ሊሆን ይችልል ።
– ከባድ ወንጀል ሆኖ ከሽርክ በታች ሊሆንም ይችላል ።
↪️ አላህን የሚገዙበት ዒባዳ የሚሆነው በካዕባ ዙሪያ በዒባዳ ንያ ሲደረግ ብቻ ነው ። ከካዕባ ውጪ በዒባዳ ንያ ጠዋፍ ማድረግ አይፈቀድም ።
↪️ ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ የሚሆነው በቀብር ላይ ወደተቀበረው አካል ለመቃረብ ተብሎ ሲደረግ ነው ። በቀብር ላይ ጠዋፍ ማድረግ በጣም አሳዛኝና አስከፊ ተግባር ከመሆኑም በላይ ጠዋፍ አድራጊው ከብዙ የአላህ ፀጋዎች የራቀ በተቃራኒው ወደ አላህ ቁጣ የቀረበ ነው ።
አላህ ለባሮቹ ከሰጠው ፀጋ ዋነኛው በካዕባ ዙሪያ ለአላህ ራሱን አስገዝቶ ወደ ጌታው በሁለመና ቀርቦ ከዐለም ከሚመጡ ወንድሞቹ ጋር ልቡ በፍሳሃ መልቶ ዒባዳ ማድረጉ ነው ። ይህን ፀጋ የሚያውቀው እዛ ቦታ ላይ ለመቆም ከጌታው የተመረጠ ሰው ነው ። ቀብር ላይ ጠዋፍ የሚያደርግ ሰው የዚህ አይነቱ ፀጋ በራሱ ላይ እርም ያደርጋል ። ልቡ በኢማን ከሞሞላት ይልቅ በሽርክና ኩፍር ጨለማ ይሞላል ።
በጣም የሚያሳዝነው አላህ የኢስላምን ፀጋ ካሳወቀው በኋላ ወደ ቀብር አምልኮ ገብቶ ፈጣሪን ከማምለክ ፍጡርን ወደ ማምለክ መሸጋገሩ ነው !!!!!! ።
ሰው አላህ ለቅናቻ ልቡ ከፍቶለት ላ ኢላሀ ኢልለላህ ካለ በኋላ መልሶ ወደ ኩፍር ጨለማ መሄዱ ምን እንደሚባል ግራ ይገባል ።
ይበልጥ የሚገርመው ይህን ተግባር ኢስላም ነው ብለው ተውሒድን ኩፍር ማለታቸው ነው ። የተውሒድ ተጣሪዎችን የነብዩን ዲን የሚያጠፉ እያሉ ስም ማጥፋታቸው ደግሞ ገርሞ የሚገርም ነው ።
↪️ ከሽርክ በታች ያለ ወንጀል የሚሆነው ደግሞ አንድ ሰው ከቀብር አምላኪዎች ጋር በጭንቅንቁ ውስጥ ኪስ ገብቶ ለማውጣት ( ለመስረቅ ብሎ) ጠዋፍ ሲያደርግ ነው ።
የሚገርመው ካዕባ ላይም ለዚህ አላማ ብሎ ጠዋፍ የሚያደርግ መኖሩ ነው ። ይህ ሰው በሁለቱም ቦታዎች ንያው ሌብነት በመሆኑ ከባድ ወንጀል ውስጥ ይገባል ።
በቀብር ላይ የሚደረግ ጠዋፍ ፍጡርን ከማምለክ በተጨማሪ የሁለት ሀገር ኪሳራ የሚያስከትል ለውድቀት ሰበብ የሚሆን ተግባር ነው ።
የኢስላም ጠላቶች ሙስሊሞችን ለማሸነፍ የነደፏቸው ስልቶች ሁሉ በእነዚያ ብርቅዬ ትውልዶች ሶሓቦች ፊት መና ሆኖ ሲቀር ። ሚስጥሩን ለማወቅ ብዙ ጊዜ ቢፈጅባቸውም መጨረሻ ላይ የእነዚያ የኢስላም የበኩር ልጆች የማሸነፍ ሚስጥር በውስጣቸው ያለው የተውሒድና የኢማን ሀይል መሆኑን ስለደረሱበት የመጨረሻውና ውጤታማ የሆኑበት እስትራቴጂ ለሙስሊሞች የቀብር አምልኮን ደጋግ የአላህ ባሮችን መውደድ በሚል አላህን ከማምለክ ሙታንን ወደ ማምለክ በማሸጋገር የቀብር አምላኪዎች ማድረግ ነበር ።
ይህ ተግባር ከአይሁዳዊው ዐብዱላህ ኢብኑ ሰበእ የሺዓዎች መስራች የጀመረ ሲሆን እስካሁንም የኢስላሙን ዐለም አጥለቅልቆ ይገኛል ።
ዐብዱላህ ኢብኑ ሰበእ የነብዩን ቤተሰቦች እንወዳለን በሚል ወደ ቀብር አምልኮ ሙስሊሞችን በማዞር የተዋጣለት ስራ ሰርቶ ለሚቀጥለው ትውልድ ሽርክን እንደ ቅርስ አበርክቶ ነው የሄደው ።
ከዛ በኋላ ሱፍዮች ይህን ቅርስ አንስተው የቁርኣንና ሐዲስን ቅርስነት ጥለው የቀብር አምላኪዎች ሆኑ ። ሙስሊሙንም ወደ አላህ አምልኮ ከመጣራት ይልቅ ወደ ወልይ የሚሏቸው የሸይጣን ወዳጆች አምልኮ ተጣሩ ። በዚህም ሙስሊሞች ከልባቸው የአላህ ፍርሃትና የኢማን ሀይል ወጥቶ ተራ የሚንቀሳቀስ አካል ሆኑ ።
በዚህም የኢስላም ጠላቶች ህልማቸው እውን ሆነ በስፋት ኢንቨስት ማድረግም ጀመሩ ። ብዙ የሽርክ ፋብሪካዎችን ከፈቱ ከኢስላም ልጆችም የሚፈልጉትን መጠን ለፋብሪካቸው ቀጠሩ ።
ቀብር አምልኮትም በሚገርም ሁኔታ የተውሒድን ቦታ አስለቅቆ ባላባት በመሆን ተውሒድ ጭሰኛ እንዲሆን አደረገው ።
አሁንም ይህ እውነታ የሙስሊሙን ዐለም አጥለቅልቆት ይገኛል ። የተውሒድ ሰራዊቶች ዋጋ ከፍለው ተውሒድን ወደ ቦታው መመለስ ይኖርባቸዋል ። ይህ ሲሆን የኢስላም ጠላቶች ይከስራሉ ሙስሊሞች የበላይ ይሆናሉ ።
አላህ በተውሒድ የበላይ የምንሆን ያድርገን ።
https://t.me/bahruteka