TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

24 Dec 2024, 14:41

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

ተስፋ አትቁረጥ!! ይልቅ ፈጣንና ብልህ ሁን!!
———
ኢማም ዐብዱል ዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
“ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም!!። የቢድዓ ሰዎች ርስበርሳቸው ይተባበራሉ ተስፋ አይቆርጡም፣ ይልቁንም በሁሉም መዳረሻዎች ወደ ጥመት ይጣራሉ፣ በማህበራዊ ሚዲዎች፣ በቲቪ፣ በጋዜጣ፣ በመፅሃፎች… ይጣራሉ። ይህ እንግዲህ ባጢል ነው። ወደ እሳት ነው የሚጣሩት። እነዚያ ወደ ጀነት የሚጣሩ ሰዎች ከነሱ የተሻለ የሚጓጉ ጀግናና ፈጣን ሊሆኑ ይገባል!!።” [አት-ተዕሊቅ ዐለ ነድወቲ ዘካት ከሚለው ካሴት]

ሸይኽ ብን ባዝ ይህን ያሉበት ወቅት ሶስት አስርተ አመታት ገደማ ነበር። ዛሬ ነገሩ ሸይኹ ከተናገሩትም በርትቷል። የቢድዓ ሰዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችንም ሆነ ሌሎችን የብዙሃን መገናኛዎችን በመጠቀም የሱንና ሰዎች እንዳይታዩና ሀቅን እንዳያሰራጩ ጥረታቸውን ተያይዘውታል። ነፍሲያ፣ ስሜትና ቡድንተኝነት የሚጋልባቸው ሰዎች ብሰዋል። በተቻላቸው ሁሉ ሱንናን ይዋጉበታል፣ እስልምና ስሙ እንጂ እንዳይቀር ይተጋሉ፣ (ምክንያቱም ቢድዐና ስሜታዊነት ሲስፋፋ እስልምና ስሙ እንጂ ተግባሩ እየቀረ ይሄዳል።) ባለ በሌለ ሀይላቸው ድፍን ጥቁር የሆነን ውሸት በሰለፊዮች ላይ በመዋሸትም ያጠለሹዋቸዋል!። የሚስኪኑን ለዲኑ የሚጨነቀውን ህዝብ ልብ አውቀው እውነት ሊመስለው በሚችለው ነገር ላይ በሱኒዮች ላይ ውሸት ቀጥፈው ያቀርቡለታል። ሀራሙን ከሀላል፣ ሀላሉን ከሀራም በማደባለቅ ያመሳስሉበታል። ሳያጣራም ይከተላቸዋል፣ እውቅናም ይሰጣቸዋል።

ከምንም በላይ እውቅናን ፍለጋና ሚዲያን ለማግኘት ይተጋሉ። ታዲያ እውቅናንና ሚዲያን ባገኙ ቁጥር ሱኒዮችን ለማጠልሸትና ሰዎች ዘንድ የሀቅ ሰዎች እንዳይታወቁ ሰዎች ወደ እነሱ ሄደው ሀቅን እንዳይማሩ ለመሸፈን፣ መንገድ ለመዝጋት ነው የሚጠቀሙት። ፈፅሞ እንግዳነትና ባይተዋርነት ተሰምቶህ ተስፋ ልትቆርጥ አይገባም!!። ይልቅ ሰበቡን ካደረስክ ዲኑን እንደሚረዳው በአላህ ላይ ፅኑ እምነት ኖሮህ ከምንጊዜውም በላይ ልትነቃና ለህዝባችን በተቻለህ ሁሉ እውነቱን ግልፅ ልታደርግለት፣ ግልፅና ተጨባጭ ማስረጃዎችን ልታስጨብጠው ይገባል። አላህን (ተባረከ ወተዓላ) በሐቅ ላይ ፅናት ልንጠይቀው፣ በሀሳብና በእውቀት በተቻለን ሁሉ ርስበርሳችን ልንደጋገፍና ልንተዛዘን ፍቅር ሊኖረን!! ልንበረታታ ይገባል!!።
✍🏻ኢብን ሽፋ t.me/IbnShifa

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

3.6k 4 24
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Наш блог Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot