Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


كناشة ابن منور

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


عَنْ عَائِشَةَ رضي الله عنها - في ذكرها لصفة صلاته صلى الله عليه وسلم - أنها قَالَتْ: "وَكَانَ يَنْهَى عَنْ عُقْبَةِ الشَّيْطَانِ".
رواه مسلم في "صحيحه" (498)


የደርስ ማስታወቂያ
~
• ኪታቡ፦ ዑምደቱል አሕካም
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6880?single
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 49፣ ሐዲሥ ቁ. 72


የወሎን ሙስሊምና የጥምቀትን በዓል ምን አገናኘው⁉️

የቦሩ ሙስሊሞች ታቦት ቢሸኙ ኑሮ ይታረዱ ነበርን⁉️

እረ ረረ ሸህ አያሌው ከበደ!

ያገሬ ዑለሞች ዱዓቶች እረ እሪ በሉ እረ ጩሁ እረ ተናገሩ እረ ኮስተር በሉ ውይ ውይ ውይ!!

https://t.me/abumuazhusenedris


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አይሁድ ወታደር ፍልስጤማዊ ህፃን ላይ የሚያደርገውን ተመልከቱ።
~
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


ደርስ
~
* መንሀጁ ሳሊኪን
* ክፍል:- 4️⃣4️⃣
* የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ
* የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


ማሳሰቢያ፦
የፖስቱ ዋና ማጠንጠኛ የዲን አስተማሪዎች ፖለቲካ ውስጥ መግባታቸው ጉዳት እንዳለው መጠቆም ነው። ያልተፃፈ እንዳታነቡ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor


ጎመን በጤና
~
አንድ እግራቸውን መስጂድ አንድ እግራቸውን ደግሞ ፓርላማ ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች ኢስላማዊ እሴቶችን እያዛነፉ የስልጣን መወጣጫ መሰላል ሲያደርጉ ዝም ማለት አይቻልም። ይሄ በኢስላማዊ እሴቶች ሂሳብ ፖለቲካዊ ትርፍ ለመሸመት የሚደረግ ግብግብ በሚነቀፍ ጊዜ "ኢስላም ፖለቲካ አይደለም ወይ?" ሲሉ የሚሞግቱ አሉ። ይህም ብቻ አይደለም "ሙስሊሙን ከፖለቲካ አርቃችሁ የማንም መጫዎቻ እንዲሆን አድርጋችሁታል" የሚል ዘልዛላ ክስ ይከሳሉ። ይሄንን የሙስሊሙን ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱንም ማህበራዊ ውቅር፣ ፖለቲካዊ ታሪክና ሁነት ያልተረዳን የተንቦረቀቀ ክስ ወደጎን እንተወውና እንዲያው ፍላጎት አለን ቢባልስ ይህንን ለማድረግ ምን አቅም አለን? ፖለቲከኞቹ እኛን ሰምተው ከፖለቲካ ሊወጡ? የማይመስል ነገር። ሲጀመር የት ያውቁንና?

ይልቅ አንድ ነገር እንጠያየቅ። እውነት ፖለቲካ የኢስላም ክፍል ነው ወይ? እንዴታ! ብቻ አስኳል ነው፣ ቅርፊት ነው የሚለውን እንተወውና ፖለቲካ ያለ ጥርጥር የኢስላም ክፍል ነው። ኢስላም መንፈሳዊ ህይወት ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን አለማዊ ህይወታችን ምን አይነት ቅርፅ መያዝ እንዳለበት ፍኖት የሚያሰምር የተሟላ የህይወት መመሪያ ነው። ስለሆነም ቤተሰባዊ ህይወት፣ ከጎረቤትና ዘመድ አዝማድ ጋር ያለ ግንኙነት፣ ማህበራዊ ጉዳዮች፣ ውርስ፣ ግብይት፣ ውልና ስምምነት ወዘተ በኢስላም ግልፅ መመሪያ የተቀመጠላቸው ጉዳዮች ናቸው። ከዚህም አልፎ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ፍትህና የአስተዳደር ስርአት እንዲሁም በመሪና በተመሪ መካከል መኖር ያለበት ግንኙነት ሁሉ መለኮታዊ መመሪያ ተቀምጦላቸዋል። እነዚህ ነገሮች ደግሞ የፖለቲካ ማእከላዊ ማጠንጠኛዎች ናቸው። እውነቱ ይህ ከሆነ ፖለቲካ ወሳኝ የኢስላም ክፍል ነው ማለት ነው።

የዘመናችን ፖለቲካ እና ኢስላም ግን ከምስራቅና ምዕራብ የራቀ ልዩነት አላቸው። ስለዚህ በደፈናው "ኢስላም ፖለቲካ ነው" አትበል። እንኳን በኢስላም ሚዛን መዝነነው እንዲሁ በሞራል መለኪያ ቢገመገም ራሱ የዘመኑ ፖለቲካ ሲበዛ ቆሻሻ አይደል'ንዴ? ፖለቲካ በአሁኑ ጊዜ የውሸት፣ የሴራ፣ የክፋት፣ የንፍቅና ተለዋጭ ስም ሆኗል'ኮ። ለጥቂቶች ስልጣን ሲባል እልፎች የሚረግፉበት፣ ለጥቂቶች ጥቅም ሲባል በህዝብ ህይወትና ደህንነት ላይ የሚቀለድበት፣ "ለሰፊው ህዝብ ጥቅም" ሲባል ህዝብን ከህዝብ የሚያባላ ስብከት የሚስሰጥበት፣ አድርባይነት የተንሰራፋበት፣ ከልባዊ ስራ ይልቅ ታይታ (Show) የነገሰበት፣ ቡድናዊ ሽኩቻ የተንሰራፋበት ሆኗል የዘመኑ ፖለቲካ። በነዚህ እድፎች ሳይጨማለቁ በፖለቲካው ውጤታማ እሆናለሁ ማለት ዘበት ለመባል የቀረበ ነው። ኢስላም ስለነዚህ ክፋቶች ምን እንደሚል ማውራት የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም።

ችግሩ እዚህ ላይ የሚቆም አይደለም። ኢስላማዊው ፖለቲካ እና "ዘመናዊው" ፖለቲካ ፍፁም ሆድና ጀርባ ናቸው። በ"ዘመናዊው" ፖለቲካ ህግ አውጪው በህዝብ ስም የተዋቀረ ሸንጎ ነው። የህዝቡን ስሜትና ዝንባሌ እያየ ህጎችን ሊቀያይር ይችላል። የህዝቡ ፍላጎት ከሆነ ወንድ ለወንድ፣ ሴት ለሴት ሊያጋባ፣ ትውልድ ገዳይ እፆችን ሊፈቅድ ይችላል። በኢስላም ደግሞ ህጉ ከአላህ የወረደ ነው። የሰዎችን ፍላጎት ተከትሎ በመፍሰስ የሚቀየር አይደለም። "ዘመናዊው" ፖለቲካ በፍትህ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ጠንካራው ደካማውን የሚሰለቅጥበት በዳርዊኒዝም Survival of the fittest "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" ቅኝት የተቀኘ ነው። Majority rule, minority right የሚሉት "ሚዛን ማስጠበቂያ" ሽንገላ እንደሆነ ለማወቅ አሜሪካና አውሮፓ ያለው የአናሳዎችን ነባራዊ ሁኔታ ለማየት አትንከራተት። እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ያለውን አሰላለፍ ማየት ይበቃሃል። የሚሻኮቱትም፣ የሚበሉትም፣ በልተው የሚያለቅሱትም "ዝሆኖቹ" ናቸው። ከነሱ ውጭ ከሆንክ ለማልቀስ እንኳ ፍቃድ ያስፈልግሃል። ባጭሩ የዘመኑ ፖለቲካ ከኢስላም ጋር ቀጥታ የሚላተሙ ብዙ ጥፋቶች በያይነቱ ታጭቀው የሚገኙበት ጎተራ ነው። እና እንዲህ አይነቱን ነው የኢስላም አካል አድርገህ የምታቀርበው? ቢያንስ ሃፍረት ይኑርሃ?

"ቢሆንም ድፍን ሙስሊምን ከፖለቲካው ማስወጣት ራስን በራስ ማጥፋት ነው። ችግራችንን ከድጡ ወደማጡ ያደርገዋል" ቢባል እውነት አለው። ነገር ግን ከዚህ "ጭቃ" ውስጥ መግባት ያለበት ማነው? የዲን አስተማሪዎች ፈፅሞ ፖለቲካ አካባቢ ዝር ማለት የለባቸውም። ምክንያቱም ፖለቲካው ብዙ መንሸራተት (ተናዙል) ይፈልጋል። የሚያስተምሩት ሃይማኖትና የሚያራምዱት ፖለቲካ ሆድና ጀርባ የሆኑ ነገሮች ስለሆኑ ተቃርኖ ውስጥ ይወድቃሉ። ክፉ ምሳሌ ይሆናሉ። አንድ ሸይኽ ወይም የመስጂድ ኢማም ከሃይማኖት ያፈነገጡ ድግሶች ላይ ባደባባይ ሲንቦጫረቅ ቆይቶ ከዚያ ደዕዋ ወይም ኹጥባ ሊያደርግ ሲቀመጥ፣ ኢማም ሊሆን ሲቀደም የሚኖረውን ስሜት አስቡት። እስኪ አንድ በፓርቲ የታቀፈ ሸይኽ የባህልና ቱሪዝም ባለስልጣን ሲደረግ በአይነ ህሊናችሁ ሳሉ። ልክ ዛሬ እንደምናየው ጥምቀት ያከብራል፣ ያስከብራል። መቼስ በፓርቲ ከታቀፍክ በኋላ ፖለቲካዊ ሹመቶችን እየመረጥክ ልትወስድ፣ እየመረጥክ ልትገፋ አትችልም። እንዲያ አደርጋለሁ ካልክ ፀያፍ ስሞችን ጀርባህ ላይ ለጥፈው በካልቾ ብለው ከፖለቲካው እልፍኝ ያባሩሃል። እና ምን ልልህ መሰልህ? ዱዓቶችህን፣ መሻይኾችህን ወደ ፖለቲካ ማዕድ የሚጋብዝ ሰው ለሙስሊሙ ያዘነ መስሎህ እንዳትሸወድ። "ጆሮውን ቆርጠው ያበሉት ውሻ፤ ስጋ የሰጡት ይመስለዋል" የሚባል ነገር አለ። ደጋግመህ አስበውማ።

በዚያ ላይ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የሀገራችን ፖለቲካ በዘር የተወጠረ ነው። የዘር ፖለቲካ ማታገያ እርሾ ደግሞ ለሌላው ዘር የሚደቅነው ጥላቻ ነው። ሊያሽሞነሙኑት ቢሞክሩም እውነታው ከዚህ ውጭ አይደለም። የሃይማኖት አስተማሪዎች ከዚህ ዘር ተኮር ፖለቲካ ጋር ሲነካኩ በርግጠኝት ራሳቸውን ያቆሽሻሉ። ከሌላው ዘር ዘንድ ያላቸው ዋጋም ይረክሳል። ይሄ ደግሞ እነሱ ላይ አይቆምም። ሰዎች ለሃይማኖት የሚኖራቸውን ምልከታም ያጠይማል። ከዚህ ይልቅ የሚያምርባቸው ያለ ልዩነት ሁሉንም እኩል ማየት ሲችሉ ነው። በዚያ ላይ የሃገራችን ፖለቲካ ያልተጠበቁ ነገሮችን በፍጥነት በማስታናገድ የታወቀ ነው። ይሆናል የተባለው ሊቀር፣ አይሆንም የተባለው ሊሆን ይችላል። ወቅታዊ ነገሮችን አይተህ ከአንዱ ወገን ብትሰለፍ ነገሮች ከምኔው ተለውጠው አጣብቂኝ ውስጥ ትገባለህ። የሃይማኖት አስተማሪ ከሆንክ ያኔ ጦሱ ለህዝብ ሊተርፍ ይችላል።

ስለሆነም መሆኑ ካልቀረ ከነሱ ይልቅ በሌላ ቢሆን ይሻላል። ችግሩ ግን እዚህም አንድ በሰፊው የሚታይ እውነት አለ። ብዙ ሙስሊም ፖለቲከኞች ከስልጣን መሰላል ላይ ያላቸው ከፍታ በጨመረ ቁጥር ከእምነታቸው ያላቸው ርቀት እየጨመረ ነው የሚሄደው። 'ኮንፊደንሳቸው' እየተሸረሸረ እየተሸረሸረ ሄዶ በኢስላማዊ እሴቶች እስከመሸማቀቅ ይደርሳሉ። "አልሐምዱ ሊላህ" ፣ "አሰላሙ ዐለይኩም"፣ "አላህ" ለማለት እንኳ የሚሳቀቁ አሉ። ፖለቲከኞቹ ቀርቶ አክቲቪስቶቹ እንኳ ባቅማቸው እውቅናቸው በጨመረ ቁጥር መልፈስፈሳቸውም በዚያው ልክ እየጨመረ ሲሄድ በቀላሉ እንታዘባለን። እነዚህ ላይ ተስፋ መጣል ከባድ ነው። ይልቁንም በእምነቱ የሚኮራ፣ ለወገኑ የሚቆረቆር፣ ጭብጨባ የማያቀልጠው ትውልድ እንዲኖረን ሁሉን አቀፍ የሞራል ግንባታ ስራ ላይ ትኩረት መስጠት ነው የሚሻለው።


ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:- 0️⃣9️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6880?single
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 44፣ ሐዲሥ ቁ. 63


አሰላሙዓለይኩም ኡስታዝ እንዴት ነህ

ከሶስት ወር በፊት ወደ ባንክ አካውንቴ በርከት ያለ ገንዘብ ስለገባ እና ባንክ ሂጄ ባናገራቸውም የግል መረጃ አንሰጥም ብለው ስለመለሱኝ የእኔ ነው የሚል አካል ካለ በዚህ ስልክ ቁጥር +251935270496 ላይ ይደውልልኝ።

ይህን አድርስልኝ፣ ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኝ ነው። ጀዛከሏሁ ኸይረን


የደርስ ማስታወቂያ
~
• ኪታቡ፦ ዑምደቱል አሕካም
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6880?single
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 44፣ ሐዲሥ ቁ. 63


የልጆች ትምህርትን የመያዝ አቅም ይለያያል። በቁርኣን፣ በኪታብ፣ በትምህርት፣ በሙያ አንዳንዶች ጎበዝ ሆነው እንደሚያስደስቱን ሁሉ አንዳንዶች ደግሞ ቀዝቀዝ ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም ልጆች አንድ አይነት አቅም ሊኖራቸው አይችልም። ስለዚህ በሌሎች ተሰጥኦ ባላቸው ልጆች እየለኩ ታዳጊዎችን ከአቅማቸው በላይ ማስጨነቅ፣ ስነ ልቦናቸውን መጉዳት አይገባም።

ከነ ጭራሹ አርግፈን እንተዋቸው ማለቴ አይደለም። ማገዝ፣ ማበረታታት፣ እንዲጥሩ መምከር፣ ሲዘናጉ መቆጣት፣ ማኩረፍ፣ እንዳስፈላጊነቱ መቅጣት ድረስ ልንሄድ እንችላለን። አንዳንዶቹ ልጆች እምቅ አቅም እያላቸው ያልታወቀላቸው ወይም እነሱም ራሳቸውን የማያውቁ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቹ በሂደት የሚለወጡ ይሆናሉ።

እንዳ'ጠቃላይ ደካማም ሆኑ ጠንካራ የሚጥሩ እና የማይጥሩ ፍሬያቸው አንድ አይደለም። አእምሮ ማለት ልክ እንደ ጡንቻ በጣረ እና በሰራ ቁጥር የሚጠነክር፣ ስራ ፈቶ ሲቆይ የሚደክም አካል ነው። ስለዚህ ልጆች ላይ ትኩረት ልናደርግ የሚገባው መጣርን፣ መታገልን ልማዳቸው፣ ባህላቸው እንዲያደርጉ እንጂ በውጤት ብቻ ልንለካቸው አይገባም። የሚጠበቅበትን አድርጎ አመርቂ ውጤት ያላመጣን ልጅ ማስተዋሉ ካለን ደካማ ጎኑን ነቅሶ በማሳየት ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ማሳየት እንጂ ማሸማቀቅ አይገባም። ብዙም ሳይጥር ውጤታማ የሚሆነውንም እንዲሁ በውጤቱ ብቻ ከመቦረቅ በጊዜ ሂደት ነገሮች በተለያዩ ምክንያቶች ሊለዋወጡ እንደሚችሉ በማስታወስ ጥረትን ልምዱ እንዲያደርግ መምከር ያስፈልጋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: فوائد الشيخ المحدث محمد زين بن الشيخ آدم الإتيوبي
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ለይተል ኢስራእ ወልሚዕራጅ

አሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም -ሐፊዞሁሏህ-

https://youtu.be/1nvShb_J9OU?si=EZ1dPaQzgz__vPT4


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ለወሎ መሻይኽ፣ ዱዓት እና ወጣቶች
~
ይህንን እያያችሁ እንዴት እንቅልፍ ይወስዳችኋል? ይሄ ወገን አያሳዝንም ወይ? ይሄው "ታቦታችን" እያሉ ነው። እነዚህ አካላት ከኢስላም ምን ቀራቸው? በጎጣቸው መስጂድ እያቃጠሉ፣ ሙስሊም እየ ~ ^ገደሉ ወሎ ላይ ሲደርስ "ዓለም ሲሰለጥን ወሎዬን ይመስላል" የሚሉት እንዲህ አይነቱን ደም እንባ የሚያስለቅስ የማንነት ቀውስ ለማስቀጠል ነው። እንዲህ ትኩረት ሰጥተው የሚዘግቡት ያለ ምክንያት እንዳይመስልህ። ወሎ የአፄ ዮሐንስ እና አፄ ምኒልክ አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻ ጥሎት ካለፈበት የማንነት ምስቅልቅል አልወጣም። እንዲወጣም አይፈለግም። ራሱም በምን ዓይነት ጫና እንዲህ አይነት ውጥንቅጥ ውስጥ እንድገባም አያውቅ።

ዱዓት እና ወጣቶች! ይህንን ወገን የማንቃት ትልቅ ኃላፊነት አለባችሁ። "ወሎ የመሻይኽ አገር"፣ "ወሎ አዝሃሩል ሐበሻ" የሚለው ራስን መደለል የትም አያደርስም። ለወገን የማይሆን ስም ቢከፍቱት ተልባ ነው፣ ጉራ ብቻ!
ከበፊቱ አንፃር ሲታይ ለውጥ እንዳለ ይገባኛል። ብዙ አካባቢ ይሄ ችግር ቀንሷል። ነገር ግን የተሻለ የሰው ኃይል ባለበት ደሴና ዙሪያዋ ላይ ይሄን ያህል አሳማሚ ነገር ማየት የመሻይኹን እና የዱዓቱን መተኛት ነው ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


ደርስ
~
• ዑምደቱል
• ክፍል:- 0️⃣8️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6880?single
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 40፣ ሐዲሥ ቁ. 69


የደርስ ማስታወቂያ
~
• ኪታቡ፦ ዑምደቱል አሕካም
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6880?single
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 40፣ ሐዲሥ ቁ. 69


አላህ አስችሏችሁ ሐጅ ለማድረግ የወሰናችሁ ወገኖች!
~
ከመምመዝገባችሁ በፊት የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ቀድማችሁ አጣሩ። ባለፈው አመት በመጅሊስ በኩል የነበረው ዋጋ በጣም ውድ ነበር። በግል ሲቆረጥ የነበረው በጣም የተሻለ ነበር። መጅሊሱ ማስቀነስ / መቀነስ ሲጠበቅበት ለምን እንዲህ እንደቆለለ አላውቅም። ለማንኛውም ዘንድሮም እንደተለመደው በመጅሊስ በኩል ያለው የትኬት ዋጋ የተጋነነ ሊሆን ስለሚችል ቀድማችሁ አጣሩ። በግል መቁረጥ ከዋጋም ባሻገር መሄጃና መመለሻ ጊዜን በተመለከተም የተሻለ አማራጭ አለው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


🎤 محاضرة بعنوان:
هل كان الصلح بين اليهود و أهل غزة دليل على النصر و العزة ؟!

الشيخ عبد المالك رمضاني


ወሊይ ማነው?
~
የአላህ ወሊዮች የታፈሩ የተከበሩ ሙእሚኖች ናቸው። ወሊይን መጥላት ከአላህ ጋር መጣላት ነው። ባይሆን ወሊይ ማለት ጀዝባ እና ገሪባ አይደለም። ወሊይ ማለት በምልጃ እና በተወሱል እያሳበበ ወደ ሙታን አምልኮ የሚጣራ ለሺርክ ጥብቅና የሚቆም ማለት አይደለም። ባጭሩ የተውሒድ ጠላት ሆኖ የአላህ ወሊይ መሆን አይቻልም።
ወሊይ ማለት አላህን የሚፈራ ሙእሚን ነው። አለቀ። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦
{ أَلَاۤ إِنَّ أَوۡلِیَاۤءَ ٱللَّهِ لَا خَوۡفٌ عَلَیۡهِمۡ وَلَا هُمۡ یَحۡزَنُونَ (62) ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَكَانُوا۟ یَتَّقُونَ (63) }
"ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም። (እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው።" [ዩኑስ: 62-63]

ስለዚህ በዚህ ቁርኣናዊ መልእክት መሰረት ወሊይነት ሁለት መስፈርቶች አሉት። እነሱም ኢማን እና ተቅዋ ናቸው። ይሄ ነው ቁርኣናዊው የወሊይ ትርጓሜ። ኢማን እና ተቅዋ ያለው ሰው ሴት ወንዱ፣ ትልቅ ትንሹ፣ ዐረብ ዐጀሙ ሁሉም ወሊይ ነው፣ ከአላህ ዘንድ። ወሊይነት በተወሰኑ አካላት ላይ የተገደበ አይደለም። ይልቁንም "ሙእሚኖች ሁላቸውም የአርሕማን ወሊዮች ናቸው።" ይሄ የኔ ንግግር አይደለም። አጦሓዊይ በአልዐቂደቱ ጦሓዊያህ ላይ ለሰፊው ህዝብ ባቀረቡት መሰረታዊ እምነት ዝርዝር ውስጥ የሰፈር ነው። እደግመዋለሁ! "ሙእሚኖች ሁላቸውም የአርሕማን ወሊዮች ናቸው!"

"የኔን ወሊይ ጠላት ያደረገ ጦርነት አውጄበታለሁ" በሚለው ሐዲሥ ስር "ወሊይ ሲባል እዚህ ላይ የተፈለገው ሙእሚን ማለት ነው" ይላሉ ነወዊይ የአርበዒን ሸርሓቸው ላይ።

ኢብኑ ከሢር ረሒመሁላህ ደግሞ ከላይ የተጠቀሰችውን የቁርኣን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦
فكل من كان تقيا كان لله وليا
"አላህን ፈሪ የሆነ ሁሉ ለአላህ ወሊይ ሆኗል።" [ተፍሲር ኢብኒ ከሢር፡ 4/278]

አማኞች እንደ ኢማናቸው እና ተቅዋቸው ልዩነት የወሊይነት ደረጃቸው ይለያያል። የነብያት እና የመልእክተኞች ወሊይነት ከተራ አማኞች ወሊይነት ጋር የሚቀራረብ አይደለም።
ወሊይነት በዘር የሚተላለፍ ንጉሳዊ ስርአት አይደለም። ይሄ የሱፊያ ሰፈር ልማድ ነው። ወሊይነት የሩቅ ሚስጥር ተናጋሪነት አይደለም። የአላህ ወሊዮች ለሸሪዐ ያደሩ ናቸው። ከሸሪዐ ያፈነገጠ ተግባር እየፈፀሙ፣ ሶላት እየተው፣ ኸምር እየጠጡ፣ ብልግና እየፈፀሙ፣ ... ከዚያ "ለምን?" ሲባሉ "ወሊዮች የተራውን ህዝብ ሸሪዐ አይከተሉም። ሌላ ስውር የራሳቸው ሸሪዐ አላቸው" የሚሉ አካላት ከነ ጭራሹ ሙስሊሞች አይደሉም። ሺርክ የሚያጨማልቁ፣ ለሺርክ ጥብቅና የሚቆሙ፣ ወደራሳቸው ወይም ወደ ሌሎች ሙታን አምልኮ የሚጣሩ፣ የሩቅ እውቀትን የሚሞግቱ አካላት የሸይ ^ጧን እንጂ የአላህ ወሊዮች አይደሉም። "ሶላት ስገዱ" ሲባሉ "ዐርሽ ላይ ነው የምሰግደው" "መካ ሐረም በርሬ ሄጄ ነው የምሰግደው" የሚሉ የዲን ሽፍታዎች ማጅራት መቺዎች እንጂ የአላህ ወሊዮች አይደሉም። ከሶላት ብቻ ሳይሆን ከጦሀራም የራቁ፣ በጤና እክል ምክንያት ወሬ የሚቀላቅሉ መጅዙቦች ደግሞ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ወፈፌዎች እንጂ ወሊዮች አይደሉም።

ሌላው ወሳኝ ነጥብ ወሊይ አይመለክም የሚለው ነው። ለጭንቅ ለችግር ሊማፀኑት የሚገባው አንድ አላህ ብቻ ነው። ወሊይ ዝናብ፣ ልጅ፣ ሲሳይ መስጠት አይችልም። ሰዎችን ከመከራ የሚያወጣውም አላህ እንጂ ደካማ ፍጡሮች አይደሉም። አላህ እንዲህ ይላል፦

{وَٱلَّذِینَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا یَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِیرٍ (13) إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا یَسۡمَعُوا۟ دُعَاۤءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُوا۟ مَا ٱسۡتَجَابُوا۟ لَكُمۡۖ وَیَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ یَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا یُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِیرࣲ (14)}
{እነዚያም ከርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ (ስሷ) ሽፋን እንኳን የላቸውም። ብትጠሯቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም። ቢሰሙም አይመልሱላችሁም። በትንሳኤ ቀንም እነሱን ከአላህ ጋር ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ-አዋቂው ማንም አይነግርህም።} [ፋጢር፡ 13-14]

ዛሬ ለጭንቅ ለችግር ይደርሱልኛል ብሎ ወሊዮችን የሚማፀን ሰው ነገ በቂያማ ቀን ጠላቶቹ ነው የሚሆኑበት። ከራሴ አይደለም የማወራው። ምስክሬ ቁርኣን ነው፦
{وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن یَدۡعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا یَسۡتَجِیبُ لَهُۥۤ إِلَىٰ یَوۡمِ ٱلۡقِیَـٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَاۤىِٕهِمۡ غَـٰفِلُونَ (5) وَإِذَا حُشِرَ ٱلنَّاسُ كَانُوا۟ لَهُمۡ أَعۡدَاۤءࣰ وَكَانُوا۟ بِعِبَادَتِهِمۡ كَـٰفِرِینَ (6) وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَیۡهِمۡ ءَایَـٰتُنَا بَیِّنَـٰتࣲ قَالَ ٱلَّذِینَ كَفَرُوا۟ لِلۡحَقِّ لَمَّا جَاۤءَهُمۡ هَـٰذَا سِحۡرࣱ مُّبِینٌ (7)}
{እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ለሱ የማይመልስለትን ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ይበልጥ የጠመመው ማነው? እነሱም (ተጠሪዎቹ) ከጥሪያቸው የዘነጉ ሆነው ሳለ?! ሰዎች (ቂያማ) በተሰበሰቡ ጊዜም ለነሱ ጠላቶች ይሆናሉ። መመለካቸውንም የሚክዱ ይሆናሉ።} [አሕቃፍ፡ 5-6]

ዱዓእ ዒባዳ እንደሆነ ልንዘነጋ አይገባም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
"الدُّعَاءُ هُوَ الْعِبَادَةُ، قَالَ رَبُّكُمُ : {ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ}"
"ተማፅኖ አምልኮት ነው። ጌታችሁ፡ {ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና} ብሏል።" [አቡ ዳውድ፡ 1479]

ተዘቅዝቆ የምታዩት የሱ ..ፊያ ወሊይ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor




ደርስ
~
• ዑምደቱል
• ክፍል:- 0️⃣7️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6880?single
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Показано 20 последних публикаций.