ሸይኽ አወልን ከሚሴን ግንባሩን ሳምልኝዛሬ ከአሶሳ አንድ ወንድሜ ጋር ተደዋወልን በእርግጥ ኑሮው አድስ አበባና ባህር ዳር ነው በቅርብ ቀን ለስራ ጉዳይ እዛ ሂዶ ነው እንጂ።
ከግል ጭውውታችን በመቀጠል እንድህ አለኝ አንተ ባቀራህው ሸርሑሱና የድምፅ ፋይል ሙራጂዐ እያደረኩ ነው።
በሸይኽ አበሉገሌ ቲርሚዚ በስልክ ደውል እየቀራሁ ነው በኡስታዝ አበሉገሌ ኢርሻድ በደውል እየቀራሁ ነው በሸይኽ አወል ከሚሴ ተፍሲሩን እየተከታተልኩ ነው አቡ ዳውድም በፅሞና እከታተላለሁ
እኔ ሸይኽ አወልን ለአሏህ ብዬ በጣም እወደዋለሁ ከምሬ ከምሬ ነው የምወደው መግለፅ አልችልም ካገኘህው
ግንባሩን ሳምልኝ አለ።
አሏሁ አክበር!!=
በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ነጋዴ ሰው በስልክ መሻይኾቹን ፈልጎ ጊዜውን ፕሮግራም አድርጎ ደርስ መከታተሉና ያላገኛቸውን መሻይኾች ተርቲብ አድርጎ ድምፃቸውን እየሰሙ ኪታብ ጋር እያነፃፀሩ ማጥናት እህጉኑ ያስቀናል አሏህ ይጨምርለት
ሲቀጥል የማታቀውን ሸይኽ ለሐቅ ብለህ በዚህ ልክ ስትወደው ያንን የቂያማ ቀኑን ጥላ ተስፋ ያሰንቃል
በሌላ በኩል የመሻይኾች ደርስ በስንቱ ሀገር እየደረሰ ሰው እየተጠቀመበት እንደሆነ አስቡት።
አሏህ ይሆ!ሐቅን አስወድደህ የሐቅ ሰዎችንም አስወድደን ሰውን ስንወድም ስንጠላም ለአሏህ እንጂ ለሌላ አያድርግብን ያረብ።
ሸይኹንም ከሚያስቡት በላይ አሏህ ዘንድ ተወዳጅ ሚያደርገው መልካሙን ስራ አሏህ ይወፍቀውና በፅናት ላይ ይቀምቅመው።
t.me/abumuazhusenedris