አሁን አሁን ላይ ሲታሰብ ምክንያታችን አፈንግጦ የወጣ ይመስላል። ወረርሽኝ ሲነሳ በዚህ ምክንያት ነው ብለን ትንታኔ ለመስጠት እንጂ ወደ አላህ ለመመለስ ስንጣደፍ አንታይም። ጦርነት መጣ ሲባል እንደለመደብን ለትንታኔ እንሯሯጣለን። የጎርፍ አደጋ ተነሳ ሲባል እንደለመደብን የለመደብንን እንጂ አላህ እያስጠነቀቀን እንደሆነ አናስተነትንም። ከዚህም ባስ ብሎ የእሳተ ጎመራ እና የመሬት መንቀጥቀጥን አብሮ አምጥቶብናል። እንደለመዱት ምክንያት ከሚተነትኑ ሳይሆኑ ካሉበት የወንጀል ጫካ ለመውጣት ለተውበት ከሚሯሯጡ ያድርገን🤲
ISLAMINDSET.