ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ቤቱ ደጅ ላይ ባለች መጠነኛ ሳጥን መጻሕፍትን ከአንዱ ወደሌሎች ማስተላለፍ ከጀመረ ከራርሟል :: ይህ ድንቅ ዓላማ በደንብ መሰራጨትና መተዋወቅ ያለበት ጉዳይ ነው ::
በእውነቱ ይህ የተዋናይ ሐሳብ በየቤቱ ሼልፍ ላይ ሳያስፈልጉ እንዲሁ የታፈኑና የተጨቆኑ መጻሕፍትን ነጻ የሚያወጣ እና የንባብ ባህላችን እንዲዳብር ራሱን የቻለ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ምርጥ መላ ነው ይዞ የመጣው :: በነጻ ወስደህ ታነባለህ ያለህን መጽሐፍ ደግሞ አምጥተህ ትስቀምጣለህ ::
በምትመለከቱት የተዋናይ ሐብታሙ ደጅ ላይ ባለችው ሳጥን ውስጥ መጻሕፍት አሉት :: ውስጥ ያሉትን መጻሕፍት ወስዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ :: እንዲሁም ደግሞ ቤታችሁ የማትፈልጓቸው መጻሕፍት ካሉ እዚች ሳጥን ውስጥ ማስቀመጥ ትችላላችሁ ::
እንግዲህ ጃዕፈር መጻሕፍትም ለዚህ ድንቅ ዓላማ በተለያየ ወቅት ከመቶ በላይ መጻሕፍትን አበርክተናል :: ይህ የወዳጃችን ሐሳብ የተወደደ ነውና ሐሳቡ የተመቻችሁ ሁሉ የሳጥኗን ይዘት ከፍ ብናደርጋት ሸጋ ነው እላለሁ ::
ስለሐሳቡ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ስለሐሳቡ ያወጉትን መስማት አሪፍ ነው ::
👇👇👇
https://youtu.be/fmSOZE2A7bU?si=IQ3OU1jF58sa-c7g
ይመቻችሁ ::