አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፣ የትግራይ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት እና የትግራይ ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የሦስትዮሽ ስምምነት አደረጉ።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፣ የትግራይ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት እና የትግራይ ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የፊርማ ሰነ- ሰርአት ስምምነት ትናንት ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል አካሂደዋል። የፊርማ ስነ-ስርአቱ በባንኩ ፕሬዝዳንት በአቶ ዳንኤል ተከስተ፣ በትግራይ ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በአቶ አሸናፊ ሃይሉ እና በትግራይ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በአቶ በሪሁ ሃፍቱ ተካሂዷል።
የዚህ ስምምነት ዓላማ የሦስቱን ተቋማት የጋራ ፍላጎትና ዓላማ ከመደገፍና ከማጎልበት በተጨማሪ የክልሉን ማህበረሰብ የቁጠባ ባህል በማዳበር ኢኮኖሚያዊ ዓቅሙን እንዲያጎለብት አስፈላጊውን የፋይናንስ አቅርቦት ለመፍጠር የተቀናጀ ጥረት ለማድረግ ያለመ መሆኑን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ባንኩ በሚያደርገው የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ ፕሮግራም ለመደገፍ ሁሉም የዘርፍ ማህበር አባላት ያላቸውን የሂሳብ እንቅስቃሴ በአንበሳ ባንክ እንዲያደርጉ እና እንዲቆጥቡ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉ የንግድ ማህበረሰብ አባላት እና ተቋማት በባንኩ መጠቀም እንዲችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እንደሚሰሩ የየተቋማቱ ፕሬዝዳንቶች ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በገፅታ ግንባታ እና ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን፤በቀጣይም የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ በሆኑ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ በስምምነቱ ተገልጿል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!