ሙስናን መከላከል እና ሰነ-ምግባርን ማስፈን አስመልክቶ ለስራ ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጠ
ስልጠናው ጥር 28 እና 29 ቀን 2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የተካሄደ ሲሆን፤ በስልጠና መርሃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የሪሶርስ ማኔጅመንት ተ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሚካኤል ገዛኢ እንደ ተቋም ሁሉም የስራ ኃላፊዎች ደንበኞችን ስነ ምግባር በተላበሰ መልኩ ማስተናገድ እንዳለባቸው እና ሙስና ዘርፈ ብዙ መሆኑን ተገንዘበው የሁልጊዜ ስራቸው መሆን እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ስነ-ምግባርን ማስፈንና ሙስናን የመከላከል ባሕላችንን አጠናክረን ማስቀጠል አለብን ብለዋል፡፡
ስልጠናው ሃገራዊ እና አለማቀፋዊ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ አስተማሪ በሆነ መልኩ የቀረበ ሲሆን፤ሙስና በባህሪውና በአይነቱ የተለያየ በመሆኑ በስራ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሙስና አይነቶችን እና ተግባራትን በስፋት እንዲያውቁ ይረዳል፡፡በዚህም በተቋሙ በሚከናወኑ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ላይ የሚያጋጥሙ ሙስና ነክ ተግባራትን ለመለየት ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው በስልጠናው የተሳተፉ የስራ ኃላፊዎች ገልፀዋል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!