ኢትዮጵያ በድጋሚ ለአጎአ ብቁ ካልሆኑ ሀገራት ተርታ መመደቧን አሜሪካ አስታዉቃለች
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ) ለመቀላቀል ፍላጎት ያላት ቢሆንም አሜሪካ ግን ይህን እድል ለማግኘት አሁንም በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታዉ ተመሳሳይ በመሆኑ እግዱ እንዲራዘም ማድረጓ ተገልጿል ።
የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ተወካይ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ለአጎአ ብቁ የሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር ለቀጣዩ በጀት አመት (2025) ሳይለወጥ እንደሚቆይ ያስታወቀ ሲሆን በድጋሚ አጎዋን ለመቀላቀል ጥረት ስታደርግ የቆየችው ኢትዮጵያ የተጣለባት እቀባ እንደገና እንዲራዘም መደረጉን ጠቁሟል ።
ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከዓመት በፊት የተጀመረዉን እና «በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘዉን የሰብአዊ መብት ጥሰት» የተመለከተዉን ጦርነት ተከትሎ እኤአ በኅዳር ወር 2021 ኢትዮጵያን ከአጎአ እንድትታገድ የሚያዘዉን ፊርማ ማኖራቸዉ ይታወቃል ።
ይህ ውሳኔው አጎአን ዓላማ አድርገዉ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሠሩ በርካታ የውጭ ኩባንያዎች እንዲወጡ ያደረገ ቢሆንም ኢትዮጵያ ግን በበኩሏ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ፊቷን ወደ ሌሎች ሀገራት ማማተር እንደጀመረች በተለያዩ ጊዜያት ስትገልጽ ቆይታለች።
capitalethiopia