አንድ የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን ተከስክሶ 38 ሞቱ
ስድሳ ሰባት መንገደኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አንድ የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን ካዛኪስታን ውስጥ ተከስክሶ 38 ሰዎች ሲሞቱ 29 የሚሆኑት ተርፈዋል። አውሮፕላኑ ከአዘርባጃን መዲና ባኩ ወደ ሩሲያ ግሮዝኒ ከተማ በማምራት ላይ እንደነበር ታውቋል። አውሮፕላኑ አቅጣጫውን በመቀየር በካዛኪስታኗ አክታ ከተማ በድንገት ለማረፍ በመሞከር ላይ ነበር። የአዘርባጃኑ ፕሬዝደንት ኢልሃም አሊየቭ የአደጋውን ምክንያት ከወዲሁ ለመናገር ባይቻልም፣ በነበረው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ለመቀየር ተገዶ ነበር ብለዋል። የሩሲያው ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በበኩሉ፣ ቀድመው የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አውሮፕላኑ ከወፎች ጋራ በመጋጨቱ ችግሩ ሊፈጠር ችሏል ብሏል። በአውሮፕላኑ ውስጥ 42 የአዘርባጃን ዜጎች፣ 16 ሩሲያውያን፣ ስድስት...
via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ኤኤፍፒ AFP))