ጥረትህን አስመዝግብ!
ፅድቅን ፍለጋ ብዙ ለፍተናል፣ ፍፁም ለመሆን ረጅም ተጉዘናል፣ በየጊዜው ለማደግ ለመሻሻል ያለማቋረጥ ጥረናል። ነገር ግን አንዳንድ ቀናት አሉ ጥረታችንን መና የሚያስቀሩት፣ አንዳንድ ሀሳቦች አሉ ልፋታችንን ትርጉም የሚያሳጡት፣ አንዳንድ ድርጊቶች አሉ በአንዴ ረጅሙን ጉዟችንን ድካም ብቻ የሚያደርጉት። በህይወታችሁ አንድ ነገር እመኑ። ሰዎች ናችሁ የተፈጠራችሁት ከስተት ጋር ነው፤ የምታዩዋቸው ሰዎችም ልክ እንደ እናንተ ሰዎች ናቸው ስህተት ይሰራሉ፣ ይወድቃሉ፣ ነገሮች ይባላሹባቸዋል። ራሳችሁ ላይ ጨክናችሁ ምንም የምታመጡት ነገር የለም። አውቆም ይሁን ሳያውቅ ስህተት ለሚሰራ ሰው ስህተቱን ላለመድገም እስከጣረ ድረስ ፈጣሪ ጥፋቱን ይቅር ማለቱ አይቀርም። ሁለት አይነት ሀጢአት አለ። የልማድና የአጋጣሚ። ከልማድ ሀጢያት፣ በቋሚነት ከሚፈፀም ስህተት የምታመልጡት በፆም፣ በፀሎትና በልባዊ ቆራጥነት ነው። ከአጋጣሚው ስህተት ደግሞ ማንነትን ሙሉ በሙሉ በመቀየር ነው። ዓለም ሁሌም ላዩን ወርቅ ውስጡን እሳት አድርጋ ብዙ የምታቀብላችሁ ነገሮች አሏት። እነዚም እናንተ ጋር ሲመጡ ስህተቶች ሆነው ይፃፋሉ።
አዎ! አትደናገጡ አትረበሹ። ፍፁም አይደላችሁም፣ ፍፁም ለመሆንም አትሞክሩ። እግዚአብሔር የሚጠላው ሀጢአትን አንጂ ሀጢአተኛን አይደለም። ስህተቱን አምኖ፣ ጥፋቱን ተቀብሎ፣ ተፀፅቶ ለተመለሰ ሁሌም በሩ ክፍት ነው። ስህተታችሁን የህይወት ዘመን ሸክም አድርጋችሁ አትኑሩ። ትናንት ብትሳሳቱ ቀሪው ዘመናችሁ ሁሉ የተሳሳተና የተመሰቃቀለ እንዲሆን አትፍቀዱ። ነገ መስራት ያለባችሁ የግል የቤት ስራ አለባችሁ፣ ዳግም እንዳይፈጠር ሊታረም የሚገባ ምግባር አላችሁ። በመጥፎ ለማድ አዙሪት ውስጥ ወድቆ ህይወቱ የጨለመበትና ተስፋ ያጣ ሰው ቢኖር ሁሌም ጨልሞ እንደሚቀር አያስብ፣ ሁሌም ጀምበር እንዳዘቀዘቀችበት እንደምትቀር አያስብ፣ ሁሌም ብሶተኛና የዓለም ተጠቂ ሆኖ እንደሚቀር አያስብ። በራሳችሁና በፈጣሪያችሁ ላይ ተስፋ ቆርጣችሁ ሰይጣንን ባለ ድል አታድርጉት፣ ራሳችሁ ላይ ጨክናችሁ የሰማይ አባታችሁን አታሳዝኑት። ስህተት አልባ ህይወት ለመኖር ራሳችሁን አታስጨንቁት። ተሳሳቱ ነገር ግን ታረሙ፣ አሁንም ተሳሳቱ ነገር ግን አሁንም ታረሙ። ስህተት መገለጫችሁ ሆኖ ፋታ ቢነሳችሁ ዝቅ ብላችሁ ከፈጣሪ ብርታትን ለምኑ።
አዎ! ጀግናዬ..! በራስ ላይ ተስፋ መቁረጥ ሽልማት የለውም፣ ራስን ችላ ብሎ መናቅ ምንም ዋጋ አያስገኝልህም። ምግባርህ ቢያሳፍርህ፣ ስራህ ስህተት ሆኖ ቢታይህ ምግባሩ አልያም ስራው እንጂ ስህተት አንተ ስህተት አይደለህም። እያወቅክም ይሁን ሳታውቅ ብታጠፋ ዳግም ራስህን የምታርምበት ሁለተኛ እድል እንዳለህ አስተውል። ሰይጣን ክፋቱ ክፉ ስራ አሰርቶ በራስህ እንድታዝን ያደርግሃል፣ ዲያቢሎስ መሰሪነቱ ብዙ ፈተና ፈትኖህ በአንዱ ቢጥልህ በዛው በአንዱ ሲኮንንህ ይኖራል። የመጡብህን ክፉ ሀሳቦች አንድ ለአንድ ታግለህ ያሸነፍክበትን ጊዜ አስታውስ። ጥንካሬህ ዛሬም እንዳለ ነው፣ አይበገሬነትህ አሁንም እንደዛው እንደተቀመጠ ነው። አንዲት ተልካሻ ስህተት በራስመተማመንህን እንድትሸረሽር አትፍቀድ፤ አንዲት ያልታሰበች ውድቀት ባዶነት እንዲሰማህ እንድታደርግህ አትፍቀድ። ከነስህተትህ ቀና በል፣ ከነጥፋትህ ደረትህን ነፍተህ ተራመድ። ነገር ግን ዳግም ያንን ጥፋት ሰርተህ የሚወድህንና የምትወደውን ፈጣሪህን ላለማሳዘን የቻልከውን ሁሉ አድርግ። ሌላው ቢቀር በእሱ ፊት ጥረትህን አስመዝግብ።
የፍቅር ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪