መሳሪያ ታጥቃችኋል!
መሳሪያ ታጥቃችኋል፣ ማንም ምንም ሊቋቋመው የማይችል አንጀት አርስ ብርቱ መሳሪያ። ከተጠቀማችሁበት ህይወታችሁን ያሻግረዋል፣ ካልተጠቀማችሁበት ስቃያችሁን ያበዛዋል። ባሻቹት ልክ ይወነጨፋል፣ እንደፈለጋችሁት ወደፊት ይመራችኋል፣ እንደ ፈቀዳችሁለት ከችግር ያወጣችኋል፣ ህይወትን ቀላልና ግልፅ ያደርግላችኋል፣ ማንም የማይሰጣችሁን ሃይልና ብርታት ያጎናፅፋችኋል። ይህ መሳሪያችሁ ምን ይመስላችኋል? የተረጋጋ አዕምሮ ነው። የሰከነ፣ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የማይበገር፣ የማይደነቅ፣ የማይሸበር የተረጋጋ፣ ሰላሙን የሚያስቀድም፣ ከሁኔታዎች በላይ የሆነ፣ ራሱን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ ራሱንም የገዛ አዕምሮ ነው። ቀላል ነገር የታጠቃችሁ እንዳይመስላችሁ። እጣፋንታችሁ በእጃችሁ ነው። የሰው ልጅ ብርቱ ነው፣ የብርታቱ ምንጭም የተረጋጋ አዕምሮው ነው። ሰሜታዊነት ከራስ አልፎ ዓለምን ሲያፈርስ ተመልክተናል፣ በሁኔታዎች አቅጣጫ መነዳት ብዙ መንገድ ሲያስት ተመልክተናል። በከባባድ የህይወት ፍንዳታዎች መሃል ሆናችሁ ምን ታደርጋላችሁ? እግሬ አውጪኝ ብላችሁ ወደ አገኛችሁት አቅጣጫ ትሮጣላችሁ ወይስ ቆም ብላችሁ የሚያዋጣችሁን አቅጣጫ ትመርጣላችሁ?
አዎ! የትኛውም ከባድ መሳሪያ ሊያመክነው የማይችል፣ ራሱን በራሱ መከላከል የሚችል ትልቅ የህይወት መሳሪያ ታጥቃችኋል። ለትንሽ ነገር አትዋከቡ፣ ለቀላል ነገር ራሳችሁን አታስጨንቁ። በምንም ሁኔታ ውስጥ መረጋጋትን ልመዱ፣ ምንም ይፈጠር ምን በፍጥነት ምላሽ ከመስጠት ተቆጠቡ። ሀሳብ ያለው አዋቂ፣ አቋም ያለው ብርቱ ሰው ለጠለቀው ሀሳቡ ጊዜ ይወስዳል፣ አቋሙን ለማራመድ ፊትለፊቱን ያጠናል። በየጊዜው ፈተና ይምጣባችሁ፣ በየሰዓቱ ነገሮች ይወሳሰቡ፣ በተደጋጋሚ ያላሰባችሁት ክስተት ይፈጠር ራሳችሁን ግዙ፣ አዕምሯችሁን ተቆጣጠሩ፣ ከባድ መሳሪያችሁን ምዘዙ፣ ሁኔታውን እንደ አመጣጡ አስተናግዱት። የዓለም አብዛኛው ህዝብ ሳያስብ የሚወስን፣ ሳያቅድ የሚያደርግ፣ የማይፈልገውን ህይወት መርጦ የሚኖር ቢሆንም እናንተ ግን አስባችሁ ወስኑ፣ አስቀድማችሁ አቅዳችሁ አድርጉ፣ በትክክለኛው መንገድ የምትፈልጉትን ህይወት መርጣችሁ የምትኖሩ አይነት ሰዎች ሁኑ። የሰው ልጅ ጥበቡም እውቀቱም አለው፣ ነገር ግን አጠቃቀሙን የማያውቅ ከሆነ ስላለው ብቻ የሚያገኘው ጥቅም የለም።
አዎ! ጀግናዬ..! ብዙዎች ቢስቁብህ ተረጋግተህ ተራ በተራ አይን አይናቸውን ተመልከት፣ ብዙዎች ሊተቹህ ቢሞክሩ ተረጋግተህ በቀጭን ፈገግታ ተመልከታቸው፣ ብዙዎች የማይገባህን ስም ቢሰጡህ ተረጋግተህ ፊትህን አዙረህ ጥለሃቸው ሂድ። ለሁሉም ነገር ተመጣጣኝ ምላሽ መስጠት ላይኖርብህ ይችላል። ምላሽህ ተመጣጣኝ ከመሆንም በላይ የሚበልጠው እንደዲሆን የማድረግ አቅሙ አለህ። እልህና ነገርን መብላት የሽንፈት ምልክት ነው። እርጋታን መገለጫህ አድርግ። አሸናፊዎች በነገር አንጀታቸውን አይበሉም፣ አሸናፊዎች ከእነርሱ ፍቃድ ውጪ በሆነ ጉዳይ ሲብሰለሰሉ አይኖሩም። በተረጋጋው አዕምሮህ እንጂ በውጫዊ ጫጫታ አትገዛ፣ በትልቁ ሀሳብህ እንጂ በጥቃቅን የሰፈር ወሬ አትመራ። ከብዙ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ድምፅ ብትሰማም ያንተውን መቼና እንዴት መጠቀም እንዳለብህ በሚገባ እወቅ። መሳሪያህ ስላለህ ብቻ የምትመዘው ሳይሆን እያለህም ቢሆን የምትጠቀምበትን ትክክለኛ ጊዜ የምትጠብቅለት ሊሆን ይገባል።