ጊዜ ይፈርዳል!
ዛሬ ከፍታ ላይ ያላችሁ፣ ዛሬ ዓለምን በመዳፋችሁ የጨበጣችሁ የመሰላችሁ፣ ዛሬ ምቾት ያንገላታችሁ፣ ህይወት የመረጠቻችሁ፣ ኑሮ የፈካላችሁ፣ በላይ በላይ ስኬት የተደረበላችሁ፣ ወዳጅ ዘመድ ፈላጊ አጨብጫቢ የበዛላችሁ አስተውሉ አንድ ቀን ዝቅ ትሉ ይሆናል፣ አስተውሉ የሆነ ጊዜ ያገኛችሁትን ሁሉ ታጡ ይሆናል፣ አስተውሉ የሆነ ሰዓት ብቻችሁን ትቀሩ ይሆናል። ዛሬ ዝቅታ ላይ የተገኛችሁ፣ ዛሬ ዓለም የናቀቻችሁ፣ ዛሬ እድል የጠመመችባችሁ፣ ወዳጅ ዘመድ የራቃችሁ፣ ግፊት ጥላቻን የተቸራችሁ፣ ሳትፈልጉ ብቻችሁን የቀራችሁ፣ ህይወት ፊቷን ያዞረችባችሁ፣ ስኬት እንደ ሰማይ ደስታም እንደ ጨረቃ የራቀቻችሁ አስተውሉ ዝቅታ መጨረሻችሁ አይደለም፣ አስተውሉ በዓለም እንደተናቃችሁ አትቀሩም፣ አስተውሉ ብቸኝነት የዘላለም እጣፋንታችሁ አይደለም። ጊዜ በጊዜው ይፈርዳል፣ ትክክለኛው ሰዓት ሁሉን ነገር ያስተካክላል። ገዢ የነበሩ ተገዢ ይሆናሉ፣ መሪ የነበሩ ተመሪ ይሆናሉ፤ በተቃራኒውም ተገዢ የነበሩ ይገዛሉ፣ ሲመሩ የነበሩ የመሪነትን ዙፋን ይረከባሉ። ስታገኙም ስታጡም፣ ስትሔዱም ስትመለሱም፣ ሲያልፍላችሁም ሲያልፍባችሁም ስሜታችሁን በልክ አድርጉት።
አዎ! ጊዜ ይፈርዳል! ጊዜ ሁሉን በግልፅ ያሳያል፣ ጊዜ ስንዴውን ከእንክርዳዱ፣ ደጉን ከክፉን፣ መልካሙን ከጎጂው ይለያል። አለኝ ብላቹ አትመፃደቁ፣ አጣው ብላችሁም አንገት አትድፉ። ሰጪም ነሺም ፈጣሪ መሆኑን አስታውሱ። ማግኘታችሁ አጥፊያችሁ ከሆነ አይሰጣችሁም፤ ማጣችሁም የሚጎዳችሁ ከሆነ ይሰጣችኋል። ችግር በዝቶባችኋል ማለት እግዚአብሔር ከሰው ሁሉ ለይቶ ይጠላችኋል ማለት አይደለም፤ ምቾት በምቸት ሆናችኋል ማለትም ፈጣሪ ከሰው ሁሉ ለይቶ ይወዳችኋል ማለት አይደለም። እያንዳንዱ ነገር የሚሆነው በምክንያት ነው። ቻዩን ፈጣሪ ያውቃል፣ ደካማውንም እርሱ ያውቃል። እርሱ የሰጣችሁን የሰጠበትን ምክንያት የሚያውቀው እራሱ ብቻ ነው። የእናንተ ድርሻ መቀበልና መቀበል ብቻ ነው። ባለስልጣኑ ባለበት ስልጣን ፈላጊ አትሁኑ፤ ፈላጭ ቆራጩ እያለ በእርሱ ስራ ጣልቃ አትግቡ። ህይወት ምርጫ ነች አንዳንድ ወሳኝ ሁነቶች ግን የፈጣሪ ገፀበረከቶች ናቸው። ሮጣችሁ ማምለጥ ከማትችሉት ነገር ስር አትሩጡ፤ መጨነቅ፣ መጠበብ፣ መዋከብ ለማያስተካክለው ነገር ራሳችሁን አታስጨንቁ፣ ራሳችሁን አታዋክቡ።
አዎ! ጀግናዬ..! ከቀረበልህ የመምረጥ ምርጫ አለህ፣ የተመረጠልህን ግን ከመምረጥ በላይ የመኖር ግዴታ አለብህ። የትናንት ድካምህ፣ የዛሬ ጥረትህ፣ የአሁን ልፋትህ ፍሬ የሚያፈራበት ጊዜ አለ። የተሻለ ነገን ቁጭ ብለህ አትመኝ፣ ያለስራ መልካም ነገር እንዲገጥመህ አትፈልግ። ጊዜ ሁላችንም ላይ ፈጣሪ የሾመብን ፈራጃችን ነው። ማንም ያልሰራውን ያገኝ ዘንድ አልታዘዘለትም፣ ማንም ያልደከመበት እንዲሰጠው አልተፈረደለትም። ዛሬ የትም ሁን፣ አሁን ምንም ስራ ነገር ግን በስራህ የምታምን፣ ነገህን መቀየር የምትችል፣ ሰው ከሚያስብልህ በላይ ፈጣሪ እንደሚያስብልህ ካመንክ በእርግጥም ምንም ነገር ሊቀየር ይችላል፣ የትኛውንም ከባድ ጊዜ ማለፍ ትችላለህ። ድህነት የህይወት ዘመን እጣፋንታህ አይደለም፣ ማጣት፣ መቸገር፣ መገፋት የተፈረዱብህ ፍርጃዎችህ አይደሉም። ላንተም ቀን እንደሚመጣ፣ ላንተም ፀሃይ እንደሚወጣ፣ ህይወትህ በአምላክ ፀጋና በረከት እንደሚታነፅ ከልብህ እመን። እየተገፋህ፣ እየተጠላህም ቢሆን ጊዜ ከፍ ያደርግሃል፤ ዛሬ ብትረሳም በሞገስ በግርማ አበይት የምትሆንበት ጊዜ ይመጣል። በራስህንም ሆነ በፈጣሪህ መቼም ተስፋ እንዳትቆርጥ።