ዋናው ነጥብ ሕይወትህን አሁን ባለበት አይነት አድርገህ የፈጠርከው አንተ መሆንህን ማወቁ ላይ ነው አሁን የምትኖረው ህይወት ያለፉት አስተሳሰቦችህና ስራዎችህ ውጤት ነው ። አንተ አሁን ላሉት አስተሳሰቦችህና አሁን ላሉት ስሜቶችህ ሀላፊ ነህ ። ለምትሰራውም ሆነ ለምትናገረው ነገር ሃላፊው አንተ ነህ ። በአእምሮህ ውስጥ ለሚመላለሰው ነገር ፣ ለምታነባቸው መፅሃፎችና መፅሔቶች ፣ ለምታያቸው ፊልሞችና የtelevision ፕሮግራሞች እንዲሁም አብረሃቸው ስለምትውላቸው ሰዎች ሃላፊው አንተ ነህ ። ሁሉም እንቅስቃሴዎች በአንተ ቁጥጥር ስር ናቸው ። በጣም ስኬታማ ለመሆን ፣ ማድረግ ያለብህ የምትፈልገውን ለማግኘት በሚያስችልህ መንገድ መስራት ነው ። በቃ ያ ነው ። ያን ያህል አስቸጋሪ አይደለም ።