ደስተኛ ሁኑ!
ሁለት ነገሮችን በፍጥነት አስወግዱ። ያለበለዚያ ህይወታችሁ እያያችሁት ምድራዊ ሲዖል ይሆናል፣ ቀስበቀስ ሰላማችሁን ታጣላችሁ፣ እያደረ ሀሳባችሁ ይቃወሳል፣ መረጋጋት ይሳናችኋል፣ ስክነት ታጣላችሁ፣ ሁነኛው የህይወት አቅጣጫ ይጠፋችኋል። እነዚህ ሁለት ነገሮች ምንድናቸው ካላችሁ፦ አንደኛ የመጥፎ ወደፊት ፍራቻ ሁለተኛ ያለፈው ጊዜ መጥፎ ትውስታ። ዛሬ ላይ ቆማችሁ የምታውቁት ሁለት ነገር ነው። ትናንተ ያለፋችሁበትንና ዛሬ ያላችሁበትን ሁኔታ። ነገን ግን በፍፁም ልታውቁት አትችሉም። ወደፊቱ የሚያስፈራችሁ ከሆነ እየፈራችሁ ያላችሁት ተጨባጭ ነገር ሳይሆን ሀሳባችሁ የፈጠረባችሁን መጥፎ ነገር ነው፣ የምትጨነቁት የእውነት በህይወታችሁ በተከሰተ ጉዳይ ላይ ሳይሆን ገና ለገና ሊከሰት ይችላል ብላችሁ በምታስቡት ስጋት ላይ ነው። አንድ ሰው ስለሚያውቀው ነገር ብቻ በጥልቀት የማሰብ ክህሎት ሲኖረው ከራሱ በላይ አካባቢውን የመግዛት አቅሙ ይኖረዋል። ስለወደፊታችሁ ብዙ ትጨነቃላችሁ? ነጋችሁ ያስፈራችኋል? በትናንታችሁ ትበሳጫላችሁ? ያለፈው ጊዜ ትውስታችሁ መረጋጋት ነስቷችኋል? በነዚህ መሃል ምን አገኛችሁ? ምንስ አተረፋችሁ?
አዎ! የማትችሉትን አትታገሉ፣ የመቀየር ስልጣኑ የሌላችሁን ነገር ለመቀየር አትድከሙ። ደስተኛ መሆን እየፈለጋችሁ በየቀኑ የደስታችሁን ጠላቶች አታሳዱ፣ የተረጋጋ ሰላማዊ ህይወት መኖር እየፈለጋችሁ ሰላም የሚነሳችሁ፣ መረጋጋትን የሚቀማችሁ ተግባር አትፈፅሙ። ሁሉም ሰው የሚኖረው ሀሳቡን ነው፤ ሁሉም ሰው የሚገዛው በሀሳቡና በፍላጎቱ ነው። ሀሳባችሁ በፍረሃት የተከበበ፣ ስጋት ያየለበት፣ ጭንቀት የተጫነው፣ መረጋጋት የራቀው፣ አዎንታዊነት የጎደለው፣ ተነሳሽነት የሌለው ከሆነ እንዴትም ደስተኛና ሰላማዊ ህይወት ልትኖሩ አትችሉም። የወደፊታችሁ ስልጣን በእጃችሁ ነው፣ ዛሬያችሁን የማስተካከል አቅሙም ብርታቱም አላችሁ። ደስተኛ ሁኑ፣ የራሳችሁን የግል ዓለም ፍጠሩ፣ በማንም ህይወት ውስጥ ጣልቃ አትግቡ፣ ትናንታችሁን ለማስተካከል አትሞክሩ፣ በወደፊቱ የሀሳብ ማዕበልም አትዋጡ። ልኩን ያወቀ ሰው ደስታው በእጁ ነው፣ አቅሙን የተረዳ ሰው የሰላሙ ጌታ ነው። መዓበል ቢመጣ አያናውጠውም፣ አውሎነፋስ ቢነሳ አያፈናቅለውም፣ ከምንም ከማንም በላይ የፀና እምነትን በራሱና በፈጣሪው ላይ አለው።
አዎ! ጀግናዬ..! የሚበጅህን ብቻ እየመረጥክ ካላደረክ፣ በሚጠቅምህ አቅጣጫ ብቻ የማትንቀሳቀስ ከሆነ ብዙ የሚጎዱህና የሚያሰናክሉህ ሁነቶች በዙሪያህ አሉ። ብዙ ምርጫ እያለህ ፍረሃትን ብቻ አትምረጥ፣ ብዙ ምርጫ እያለህ በቁጪትና ፀፀት መንገድ አትመላለስ። ዓለም የሰጠችህን ሁሉ አትቀበል፣ ሰው ባዘጋጀልህ መንገድ ብቻ አትጓዝ። ቀብረር በል፣ ደረጃህን ጨምር፣ እርከንህን አሳድገው፣ ትንሽም ቢሆን ራስህን ቆልል፣ ከፍ አድርገው። ለዓመታት ለሰው ደስታ ለፍተህ ከሆነ አሁን ትኩረትህን ወደራስህ ደስታ አዙረው፣ ለረጅም ጊዜ በማታውቀው የሀሳብ ውቂያኖስ ውስጥ እየዋኘህ ከነበረ አሁን ራስህን ከዛ ውስጥ አውጣ። ወርቁ በእጅህ እያለ መዳቡን ፍለጋ ራስህን አታስጨንቅ፣ መሪህ ሆነህ ለመመራት አትዘጋጅ። ደፋር ደፋር የሆነው የሚገጥመውን ሁሉ ስለሚያውቅ አይደለም፣ ይልቁንም የሚገጥመውን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ስለሆነ እንጂ። ፍረሃትህን በፍረሃት አስታግስ፣ ደስታህን ከትናንትም ከነገም ነጥለው፣ የምትፈልገውን ዓለምም ለራስህ ፍጠር።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን!
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro