ሰው በሁለት ነገሮች ተጠምዶ ህይወቱን ያባክናል። ወይ በበታችነት ስሜት ወይ ደግሞ በበላይነት ስሜት ይሰቃያል፡፡
አንድ ሰው በበታችነት ስሜት ከተያዘ ውስጡ በጥልቀት ይታመማል፡፡ ከንቱ እንደሆነ እያሰበ ከኖረ በህይወት የመቆየቱ ጉዳይ አስቸጋሪ ይሆናል። በህይወት እየኖረ ቢሆንም ሙት ነው። እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በህይወት የሚቆዩ በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ አብዛኞቹ ግን ከመሞታቸው በፊት የሚሞቱ ናቸው፡፡ በሰባ አመታቸው ቢቀበሩም የሞቱት ግን ቀደም ብለው ነው፡፡ በሞታቸውና በቀብራቸው መሀል የሰላሳ፣ የአርባ ወይም የሃምሳ ዓመታት ክፍተት ሊኖር ይችላል፡፡
በዙሪያችሁ የተንሰራፋውን ግዝፈተ ተፈጥሮ ስትመለከቱ የበታችነት ሊሰማችሁ ይችላል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ሰው ምንም ነው፡፡ በውቅያኖስ ሞገዶች ላይ እንደተንሳፈፈ ገለባ ነው፡፡ ምንም አይነት ሃይልም ሆነ አቅጣጫ የለውም፡፡ እንደዚህ አይነት የበታችነት ስሜት አይምሮን ጨምድዶ ከያዘ የሰው ህይወት በመከፋት የተሞላ ይሆናል፡፡ በህይወት የሚኖር ሙት ይሆናል። ህይወቱ አመድና ትቢያ ይሆናል። የህይወታችሁ ነበልባል ከውስጣችሁ ከጠፋ፣ የፋኖሳችሁ ነበልባል ከጠፋ፣ በፀሃይ ብርሃንም ምንም ማድረግ አትችሉም፡፡ ለናንተ ፀሃይ ምንም ጥቅም አይኖራትም፡፡
በሰው ውስጥ መላው ግዝፈተ ተፈጥሮ እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል። በሰው ውስጥ መለኮት እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ሰው የበታች አይሆንም፡፡ በጣም የሚገርመው ሰው የበታችነት ስሜቱን ለማውደም አስቦ በየበላይነት ስሜት መጃጃሉ ነው፡፡ የበታችነት ስሜቱን ለማፈን የተለያዩ መንገዶችን መፈለግ ይጀምራል። ውስጡን የበታችነት ስሜት ሲሰማው ሃብት በማከማቸት ለአለም ህዝብ ከንቱ አለመሆኑን ሊያሳይና ከሌላው የበላይ የመሆን ስሜት ሊሰማው ይችላል። ከየበታችነት ስሜቱ የተነሳ ጭንቅላቱ ላይ ዘውድ ደፍቶ ከንቱ አለመሆኑን ለማሳየት ይሞክራል። የበላይነት ፉክክር ውስጥ የሚከተው የበታችነት ስሜት ነው፡፡ እናም የበላይ ለመሆን በሚደረግ የእብዶች እሽቅድምድም ውስጥ ያሉ ሰዎች ያለጥርጥር ውስጣቸው በየበታችነት ስሜት እየተሰቃየ ነው ።