ምግብህን ምረጥ!
ወደ ውስጥህ የምታስገባውን ፣ እንዲነዳህና እንዲቆጣጠርህ የምትፈቅድለትን የአዕምሮ ምግብ በሚገባ ምረጥ ። የተመረዘ ምግብ ጤናህን ይመርዛል ፣ ለአካላዊ ህመም ይዳርግሃል ፤ የተመረዘ ንግግር ፣ የጥላቻ አመለካከት ፣ ኋላቀር አስተምህሮ ፣ የፀባጫሪነት ትርክት ፣ ጭፍን ጥላቻ ደግሞ አዕምሮህን ሚዛን ያሳጣዋል ፤ መንፈሳዊ ህይወትህን ያዛባዋል ፤ አስተሳሰብህን ዋጋ ቢስ ያደርገዋል ፤ በተደጋጋሚ ለስህተት ይዳርግሃል ፤ ውድቀትህን ያፋጥነዋል ፤ በትንሹም በትልቁም በእራስህ እንድታዝን ያደርግሃል ። አንተ ያልተጠነከክለት አዕምሮህ በፍፁም ሊጠነቀቅልህና የተሻለ ለምትለው ስፍራ ሊያበቃህ አይችልም ።
አዎ! ጀግናዬ..! ምግብህን ምረጥ ፤ አዕምሮህ ውስጥ የሚቀረውን ፣ ከአስተሳሰብህ ጋር የሚገናኘውን ፣ ትኩረትህን የሚስበውን ፣ ስሜትህን ሊነዳ ፣ ህይወትህን ሊቆጣጠር የሚፈልገውን የትኛውንም አስተምህሮም ሆነ ንግግር በጥንቃቄ ተቀበል ። በምንም መንገድ ያልሰማሀው ፣ ያላነበብከው ፣ ጆሮ ሰተህ ያላዳመጥቀው ፣ በትኩረት አስበህበት ያልተከታተልከው ነገር በተግባርህ ሲገለጥ ልታየው አትችልም ። አስተሳሰብህ በሙሉ የምታየው ፣ የምትሰማው ፣ የምትከተለው ፣ ትኩረት የምትሰጠው የእያንዳንዱ ግብዓትህ ውጤት ነው ። ከአንድአይነት ተግባር የተለየ ውጤት እንደማይጠበቀው ሁሉ ፣ አንድአይነት ነገር አዕምሮህን እየመገብከው የተለየ ውጤት ልታመጣ አትችልም ። አዕምሮህ የተቀበለውን ብረሃን እንደሚያንፀባርቅ መስታወት ነው ። ጠቃሚ ይሁን ጎጂ የሰጠሀውን ሊሰጥህ ሁሌም ዝግጁና ትጉ ነው ።
አዎ! መሬት የዘራሀውን ዘር ያበቅልልሃል ፤ ስንዴን ብትዘራ ስንዴውን በተሻለ ምርት ያበረክትልሃል ፣ ገብስንም ብትዘራ እንዲሁ ያደርጋል ። ምድር በእግዚአብሔር ድንቅ ጥበብ የሰጠሀውን መልሶ አብዝቶ መስጠቱ ግብሩ ነው ፤ ስራው ነው ። አዕምሮም ከዚህ የተለየ ተግባር የለውም ። የዘራህበትን በእጥፉ ያሳጭድሃል ። በልጅነታችን የተዘራብን አትችልም ፤ ፈሪ ነህ ፣ ነውር ነው ፣ ሰው ምን ይልሃል ፣ ጎመን በጤና ፣ የእንትና ዘር ዘርህን እንደዚህ አድርጓል ፣ በዚህ ዘመን ዘመዶችህን እንዲ ያደረጉት እነርሱ ናቸው የሚሉ አመለካከቶችና አስተምህሮዎች ከእድሜያችን ጋር አብረው ያድጋሉ ፣ ከፍ ስንል ፍረሃታችንም ይጨምራል ፤ የይሉኝታ አጥራችን ይጠነክራል ፤ የጥንቃቄያችን ብዛቱ ከሙከራ ያግደናል ፤ ባላየው ይባስም በማይጠቅመን የክፋት ታሪክ ታስረን ፣ ቂምን አንግበን ፣ ቁጪትን ታቅፈን የእራሳችንን ህይወት በአግባቡ ሳንኖር እናልፋለን ። ህይወትህ ውድና አንድ እንደሆነች አስታውስ ። የሚመራትን አዕምሮህን በሚገባ ጠብቀው ፣ ተንከባከበው ፣ ከለላ ሁንለት ። በሆነ ባለሆነው አታዋክበው ፣ ትኩረቱን አትረብሽ ፣ ሰላሙን አታናጋ ። የትኛውንም ነገር መርጠህ አቀብለው ።