ግድየለም አመስግኑ!
ችግር ውስጥ ናችሁ? ከነ ችግራችሁ አመስግኑ፣ ፈተና ገጥሟችኋል? ከነፈተናችሁ አመስግኑ፣ ድካማችሁ ፍሬ አላፈራም? ሀሳባችሁ አልሞላም? እቅዳችሁ አልተሳካም? ስራችሁ አልሰመረም? ውጥናችሁ ከዳር አልደረሰም? ባልጠበቃችሁት መንገድ ተገፍታችኋል? ብቸኝነትና ጭንቀት ፋታ ነስቷችኋል? ምንም ውስጥ ሁኑ ግዴለም አመስግኑ፣ ምንም ይግጠማችሁ ዝም ብላችሁ በህይወት ስለመኖራችሁ ደስተኛ ሁኑ። አንዳንድ ነገሮች በእናንተ ላይ ቢከሰቱም የመቀየር ስልጣኑ ላይኖራችሁ ይችላል፣ አንዳንዱ ሁነቶች መሆን ስላለባቸው ብቻ ሊሆኑባችሁ ይችላል። ነገር ግን ሁሉም ነገር አላፊ ነው። ከየትኛውም ችግር የከፋ ችግር አለ፣ ከማንኛውም ህመም የሚበልጥ ሌላ ህመም አለ። እነዛ በብዙ ችግር መሃል ሆነው፣ እነዛ አጣብቂኝ ውስጥ ሆነው እንኳን "ተመስገን" የምትለውን ቃል ያልዘነጉ፣ ካጡት በላይ ያገኙንተን የሚቆጥሩ፣ በፍቃዳቸው በተስፋ የሚሞሉ፣ መርጠው ፈጣሪን የሚያመሰግኑ ሰዎች ከማንም በተሻለ ህይወትን ቀለል አድረገውና ተደስተው ይኖራሉ። የአሁን ሁኔታችሁን እያማረራችሁ የባሰው አትጥሩ፣ በአሁኑ ከባድ ሁነት እየተበሳጫችሁ የበለጠውን አትሳቡ።
አዎ! ግድየለም አመስግኑ፣ ግድየለም ባላችሁ ተደሰቱ፣ ግድየለም በትንሹም በትልቁም አታማሩ። ባላችሁ ለማመስገን ቅጣት እስኪመጣባችሁ አትጠብቁ። የሰው ልጅ ምንም የሚወዳደርበት ነገር ቢጠፋ እንኳን በችግር መወዳደር የለበትም፣ በህመም መነፃፀር የለበትም። ባላችሁ ለማመስገን የግድ እናንተ ያላችሁ ነገር ሌላው የሌለው ነገር መሆን የለበትም። በዚህ ሰዓት ሌላ ቦታ መሆን እንደነበረባችሁ እያሰባችሁ የምትጨነቁ ከሆነ ቆም በሉ፣ አሁን የምትኖሩት ኑሮ የማይገባችሁ እንደሆነ እያሰባችሁ ከራሳችሁ ጋር የምትሟገቱ ከሆነ ቆም በሉ፣ አሁን አብሯችሁ ያለው ሰው እንደማይመጥናችሁ እያሰባችሁ እርሱን ለመውቀስ የምትሞክሩ ከሆነ አሁንም ቆም በሉ። የበዛው ሀሳብና ጭንቀታችሁ መቼም ነፃ አያወጣችሁም። ይልቅ በቅድሚያ የሚያስጨንቃችሁ ነገር ላይ ያላችሁን ስልጣን መርምራችሁ እወቁ፣ ከእናንተ የሚጠበቀው ሁሉ ስለማድረጋችሁ በቅድሚያ እርግጠኛ ሁኑ።
አዎ! ጀግናዬ..! ምስጋናም ሆነ ማማረር የምርጫ ጉዳይ ነው። ማንም እንድታመሰግን አያስገድድህም፣ ማንም ካላማረርክ ብሎ እጅህን አይጠመዝዝህም። ሁለቱም አማራጭ በእጅህ ነው። ማንም ሰው ቢታመም ራሱ መድሃኒቱን ፈልጎ ካልዋጠ ሊድን አይችልም። በብሶትና በምሬት የቆሰለ አንጀትም እንዲሁ መድሃኒቱ ምስጋና ብቻ ነው። ካንተ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ነገር ራስህን አታማር፣ ዋናው በህይወት የመኖር ስልጣን ተሰጥቶህ በትርፍ ነገር ውስጥህን አታውክ። ቢሆንለት ማንም ሳቅና ደስታን አይጠላም፣ ቢሳካለት ማንም ምስጋናና ውዳሴ የሚረብሸው የለም። ነገር ግን የምታመሰግነው ሲሆንልህ ብቻ አይደለም፣ የምትደሰተው ሲሳካልህ ብቻ አይደለም። አንተ የማታውቀው የከፋ ነገር በትንሽ ሀዘን ሲያልፍልህ ማመስገን ይኖርብሃል፣ ለቀጣይ ስኬት የሚያመቻችህ የአሁን ማጣትና ውድቀት ሲገጥምህ መደሰት ይኖርብሃል። ለጭንቀትና ሀዘን ምክንያት ከምትፈልግ ለደስታና መረጋጋትህ ምክንያት ፈልግ፣ የሚያማርሩና የሚያበሳጩ ክስተቶችን ከምትቆጥር የሚያስመሰግኑና የሚያስወድሱ በረከቶችህን ቁጠር።