ሽንተፈታችሁን አታውጁ!
ደካሞች ሁሌም ተሸናፊዎች ናቸው። ትልቁ ችግራቸውም ሽንፈታቸውን አምኖ አለመቀበላቸው ነው። ተሸናፊዎች ተቀባይነት ሲነፈጉ ተቀባይነት ለማግኘት ያላቸው ፍላጎት ይበልጥ ይጨምራል፣ በሰው ሲገፉ በግድ ሰውን ለመቆጣጠርና ለመግዛት ይሞክራሉ፣ በምንም መንገድ ሽንፈትና ውድቀታቸው እንዲታወቅባቸው አይፈልጉም። አንድ ሰው ካልፈለጋችሁ ለነገሩ የማይሆን ምክንያት እየደረደራችሁ አታወሳስቡት፣ አንድ ሰው ካልመረጣችሁ በግድ እንዲመርጣችሁ ለማድረግ አትሞክሩ። አንዳንዴ ብዙ እያወቁ እንዳላዋቂ ማለፍ ጥበብም ብለሃትም ነው። አለመፈለግ የማንም ሰው እጣፋንታ ሊሆን ይችላል፣ በሰው ዘንድ ተቀባይነት አለማግኘት ማንም ላይ ሊከሰት ይችላል። እውነታውን ለመሸፋፈን አትጣሩ፣ የሆነባችሁን እንዳልሆነ ለማድረግ አትድከሙ። በፍፁም ደከሞችና ተሻናፊዎች የሚያደርጉትን የሰነፍ ስራ አታድርጉ። አንዳንድ ሽንፈቶቻችሁ ሽንፈት የሚሆኑት እናንተ መቀበል አቅቷችሁ በምታስመስሉበት ጊዜ ይሆናል። ምንም በሌለበት ስሜታችሁን ብቻ እየተከተላችሁ አትድከሙ፣ የትም ብትሔዱ ወደ ህይወታችሁ የሚመለሰው ራሳችሁ ያደረጋችሁት ነገር እንደሆነ አስተውሉ።
አዎ! ሽንፈታችሁን አታወቀጁ፣ ድክመታችሁን አደባባይ አታውጡ፣ ስንፍናችሁን ለዓለም አታሳዩ፣ ውድቀታችሁን አታሳውቁ። ባላወቃችሁትና ባልገባችሁ መንገድ ራሳችሁ ላይ አትጨክኑ። ብቸኝነት ብርቅ አይደለም፣ አለመፈለግ አለመወደድ አዲስ አይደለም፣ ተቀባይነት ማጣት ብርቅ አይደለም። የትኛውም ከባድ ነገር ሲገጥማችሁ እናንተ ላይ ብቻ እንደተከሰተ አድርጋችሁ ማሰባችሁን አቁሙ። ዓለም በብዙ አጥቂዎችና ተጠቂዎች የተሞላች ነች፣ ምድር ላይ በጣም ብዙ ጎጂዎችና ተጎጂዎች አሉ። ስለመጠቃታችሁ፣ ስለመጎዳታችሁ፣ ስለመገለላችሁና ለብዙ በደል ስለመዳረጋችሁ ደጋግማችሁ ማውራት የጀመራችሁ እለት አስከፊውን አይወድቁ አወዳደቅ ትወድቃላችሁ፣ ለመጥፎው የከፋ ሽንፈት ትዳረጋላችሁ። ዓለም ላይ ብዙ ደካማና ልፍስፍስ ሰው ሊኖር ይችላል፣ ከሁሉም በላይ ግን በጉልበቱ እንደሚተማመን፣ ያጣውን ነገር ሁሉ በግድ ለማግኘት እንደሚጥር ሰው ልፍስፍስ ሰው የለም።
አዎ! ጀግናዬ..! በገዛ ፍቃድህ ፀጋህን አትግፈፍ፣ ወደህ ደካማና ልፍስፍስ አትሁን። በትንሹም በትልቁም እልህ ውስጥ አትግባ። አንዳንድ ነገሮችን ባላየ ባልሰማ ማለፍን ተለማመድ። ለማንም እንዳስቀመጠህ አትገኝለት፣ ከተሰጠህ ቦታ ከፍ በል፣ ነው ተብለህ ከምትታሰብበት እርከን ውጣ። የህይወት አቅጣጫህን ሰው ሳይሆን ራስህ ምረጥ። ፊት የነሱህን ሰዎች እየተከተልክ ዘመንህን አትፍጅ፣ የማትፈለግበት ስፍራ እያንዣበብክ ዋጋህን አታሳንስ። ራስን ሆኖ መገፋት ውርደትም ሆነ ውድቀት ሊሆን አይችልም፣ በራስ ምርጫ ተቀባይነት ማጣት ምንም የሚያሳፍር ነገር የለውም። ሲሔዱ መውደቅ እንደመኖሩ ሲጠይቁም እምቢ መባል ያለ ነው። "የወደድኩት አልወደደኝም፣ ያከበርኩት አላከበረኝ፣ የመረጥኩት አልመረጠኝም" ብለህ ራስህን ጫና ውስጥ አትክተት። ቆፍጠን ብለህ የመጣውን እንደ አመጣጡ አሳልፍ፣ በምትሰጠው ያልተገባ ምላሽ ድክመትና ሽንፈትህን አጉልተህ አታሳይ። እያመመህም ቢሆን መቻልን፣ ተቸግረህም ቢሆን በራስህ መወጣት መቻልህን አሳውቅ።