እስኪ እየው!
አንድ ቀን ብቻ፣ ለተወሰነ ሰዓት፣ ለጥቂት ደቂቃ ብቻ የሚፈልጉትን ማግኘት፣ የሚፈልጉበት መድረስ፣ የተመኙትን ማግኘት ምን እንደሚመስል በአይነ ህሊናህ ተመልከተው። ሰላሙን ማጣጣም ጀምር፣ ስሜቱን ወደ ውስጥህ አስገባው፣ ወደ እራስህ ተመልከት፣ ለማን እስከምን መትረፍ እንደምትችል አስብ። ይህን እንዳታደርግ የሚከለክሉህ ብዙ የደመና ግርዶሽ የመሰሉ መሰናክሎች ይኖራሉ። ነገር ግን ማየቱን ሊከለክሉህ አይችሉም። አይነ ህሊናህ ሲበራ፣ ውስጥህ ሩቅ ሲመለከት፣ በተስፋ ስትሞላ በእይታህ ብቻ ለእራስህ አለኝታ መሆን ትችላለህ፣ በአመለካከትህ ብቻ ዋጋህን ከፍ ማድረግ ትችላለህ። የሩቁን አቅርቦ መመልከት፣ የሚፈልጉትን ወደ እራስ ማምጣት፣ የልብን መሻት በዙሪያ ማስቀመጥ ቀላል ጉዳይ አይደለም። ለዚህም ነው ብዙዎች ሲያደርጉት የማይታየው።
አዎ! ጀግናዬ..! እስኪ እየው፤ ፍላጎትህ ሲሆን ተመልከተው፤ እቅድህ ሲሳካ አጣጥመው፤ አላማህ እውን ሲሆን ህልምህን ስትኖረው ይሰማህ። በእርግጥም ስሜቱ ልዩ እንደሚሆን ግልፅ ነው። ነገር ግን ወደ ትክክለኛው መዳረሻህ ለመድረስ ስሜትህ ከእምነት ጋር ሊዋሃድ ይገባል፤ እይታህ በሃሳብና በፍላጎትህ ሊቃኝ ይገባል። በምናብህ የምትመለከተው ነገር ከሰማይ የወረደ ወይም ከምድር የፈለቀ አይደለም። ካንተ ከእራስህ፣ ከፍላጎትህ፣ ከምርጫህና ከሃሳብህ የመጣ ነው። የማትፈልገውን ነገር ደጋግመህ እያደረክ የምትፈልገውን ውጤት እንደማትጠብቀው ሁሉ ሃሳብህም ከዚህ የተለየ ነገር አያጎናፅፍህም። የምታስበውን ነገር በምናብህ ትመለከታለህ፤ የምትናፍቀው ነገር ደጋግሞ ወደ አዕምሮህ ይመጣል።
አዎ! ከማትፈልገው ህይወት ጋር መታገል አቁም፤ በማትፈልገው ሁኔታ መበሳጨት አቁም፤ ከማያስደስትህ ትግባር ፋታ ውሰድ። የምትፈልገውን ስታደርግ ደጋግመህ እራስህን ተመልከት፤ በሂደት በእውን እርሱን ማድረግ ጀምር። ህይወትን ሁለት ወዶ ማሸነፍ አይቻልም። ወይ ምቾትህን ወይ ወደፊት እንዲሆንልህ የምትፈልገውን ነገር መምረጥ አለብህ። ዛሬ እንደምትኖረው ምቾት በሚመስል የድግግሞሽ አለም መኖር ትችላለህ፤ አልያም እንደምንም ጨክነህ በአይነ ህሊናህ ደጋግመህ ለምትመለከተው ህይወት መሱዓትነት መክፈል ይጠበቅብሃል። አደጋ አለው እውነት ነው፤ ያስፈራል እውነት ነው፤ እንደሚታሰበው ቀላል አይደለም እውነት ነው። ነገር ግን ትልቅ ውጤት አምጥቶ አደጋ የሌለው፣ ሳያስፈራ የሚሞከር አዲስ ነገር፣ ቀላል ሆኖ የሚገነባህና የሚያጠነክርህ ነገር ፈፅሞ እንደሌለ ማወቅ ይኖርብሃል። በምናብህ የተመለከትከውን ታላቅነት በአደጋ ውስጥ በማለፍ፣ ከባዱን ሁኔታ በመጋፈጥና እቅድህን በልበሙሉነት በመከወን እውን አድርገው።