ጨለማውን ግፈፉት!
እናንተ ጋር ብረሃን አለ ማለት ዓለም በሙሉ በብረሃን ተጥለቅልቃለች ማለት አይደለም፣ እናንተ ጋር ፀሃይ ወጣች ማለት ብዙዎችም የፀሃይ ብረሃን ያገኛሉ ማለት አይደለም። እናንተ ጋር የዘነበ ዝናብ በቅርብ ርቀታችሁ ላይዘንብ ይችላል፣ እናንተን ያስደሰተ ጉዳይ ለብዙዎች ትርጉም አልባ ሊሆን ይችላል። ህይወት የግል ነች ስሜት ግን የጋራ ነው። ለራሳችሁ ትኖራላችሁ እናንተ የሚሰማችሁን ስሜት ግን ሌሎችም እንዲሰማቸው ትጠብቃላችሁ፣ የናንተ ቤት ብረሃን ሁሉም ሰው ቤት ያለ ይመስላችኋል፣ ለእናንተ ስላለፈላችሁ ለብዙዎች ያለፈላቸው ይመስላችኋል። እናንተ በፍቅር፣ በደስታ፣ በሃሴት፣ በስኬት መኖር በፍቃዳችሁ እስካላጋራችሁት ድረስ የእናንተና የእናንተ ብቻ ነው። የአብዛኛውን ሰው ህይወት በእናንተ ህይወት አትለኩ፣ የአብዛኛውን ሰው ገቢ በእናንተ የገቢ መጠን አታስቡት። ምድር ለዘራው ሁሉ ፍሬ ብታፈራም ህይወት ግን ለሚዳክረው ሁሉ እኩል እንደማትክሰው አስተውሉ። የእናንተ ብረሃን የእናንተ ብቻ ነው፣ የእናንተ ስኬትም የእናንተ ብቻ ነው። ነገር ግን እኔ ተመቾቶኛል ብላችሁ ሌላውን አትውቀሱ ወይም አትወንጅሉ።
አዎ! ጨለማውን ግፈፉት! ብረሃን አጥቶ በጨለማ ለሚዳክረው፣ ህይወት ከብዶት ላይ ታች ለሚለው፣ ግራመጋባት አዕምሮውን ላናወዘው፣ በሰው ተከቦ ሰው ለተራበው፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሮች የተወሳሰቡበትን ያንን ሰው ጨለማውን ግፈፉለት፣ የብረሃንን ፀዳል አስመልከቱት፣ የህይወትን ውበት አስጎብኙት፣ ንፁህ ፍቅርን አካፍሉት፣ ከበረከታችሁ አቋድሱት፣ ከእናንተ በላይ በእናንተ መልካም ስራ ፈጣሪው እንዲያመሰግን አድርጉት። የሰው ልጅ ትልቁ ትርፉ ሰው ነው። ደስታም ይሁን ስኬት ሙሉ የሚሆነው ሲያካፍሉት ነው። ሰው በሰውነቱ ብቻ ባለፀጋ ነው፣ ሰው በተፈጥሮው ብቻ አለቃ ነው። በህይወት መንገድ ከፍታም ዝቅታም ያለና የሚኖር ነው። ከፍ ስትሉ አፈር አይንካኝ ዝቅ ስትሉም ኑሮ መረረኝ አትበሉ። ረጅም እድሜ ስትኖሩ ሁሉ ታዩታላችሁና ታገሱ። ስላላችሁ ምድሩን ሁሉ ለማሰስ አትሞክሩ ስላጣችሁም አንድ ቦታ ታስራችሁ አትቀመጡ። አንዳንዶች ቢያተርፉ የእናንተም ትፋማነት አይቀርም፣ አንዳንዶች ከተሳካላቸው ለእናንተም አንድ ቀን መሆኑ አይቀርም።
አዎ! ጀግናዬ..! ያለህን ሁሉ ለማሳየት ደረትህን አትንፋ፣ ያንተን ስኬት ከሰው አትጠብቅ። ደስታንም ሆነ ስኬትን አንተ በምትፈልገው ልክ ታገኘዋለህ ሌላውም እንደዛው በሚፈልገው ልክ ያገኘዋል። አንተ ብዙ ዋጋ ከፍለህ በእጅህ ያስገባሀው ድል ለሌላ ሰው ብዙም ትርጉም ላይሰጥ እንደሚችል አስብ። ከሰው እየተለካኩ፣ ሰው ፊት ራስን እየሰቀሉ፣ በትንሽ ስኬት እንደ የዓለም ገዢ ራስን እየቆጠሩ ህይወት አይገፋም፣ ኑሮ ትርጉም አይኖረውም። የእውነት አቅሙ ካለህ ለብዙ ችግረኛ ድረስ፣ ውስጥህ የምር የሚፈልገው ከሆነ ለንተ የበራልህን ብረሃን ለሰዎችም አብራ። ራስህን ብቻ ለማስደሰት እየለፋህ፣ የለት ጉርስህን ብቻ ለማግኘት እየተጋህ፣ የግል ቤትህን ብቻ ለመገንባት እየደከምክ እንዲሁ ባክነህ አትለፍ። ከምንም በላይ ራስህን ለማጎልበት ታገል፣ የብዙሃኑን ጨለፈማ ለመግፈፍ ተፋለም፣ የወገንህን እስራት ለመፍታት ራስህ ሰዋ። ሰው ሆነህ ሰውን አትርፍ፣ በግልህ ከምትገለገልበት እቃ በላይ ብዙዎች የሚገለገሉበትን የላቀ አስተሳሰብ ለሰዎች አሸጋግር። ድልህ የብዙዎች ድል ይሆን ዘንድ የትግልህን ጀማሮ ምክንያት የጋራ አድርገው።