ማንን አስቀደምክ?
"ነፍስ የምትሞተው በሃሳቧ ቀለም ነው። " - Marcus Aurelius
ሃሳብ ነፍስን የማደህየትም የማበልፀግም አቅም አለው። ውስጣችን በሚንሸራሸረው ሃሳብ ወይ እናተርፋለን ወይም እንጠፋለን። ነፍስህን ከማያንፁ ሃሳቦች የመጠበቅ ሃላፊነት አለብህ፣ ማንነትህን ከሚረብሹህ እሳቤዎች ማቀብ ይኖርብሃል። ሁሉን በአንድ መስራት ባትችል የምትሰራውን ግን ቅድመተከተል ማስያዝ ትችላለህ፤ ሃሳብህን መቆጣጠር ባትችል በእርሱ ላይ ግን እራስህን ማንገስ ትችላለህ። የእያንዳንዱ ሰው ህይወት በመሪው የሚወሰን ነው። ይመሩን ዘንድ ሙሉ መብት የሰጠናቸው አካላት የህይወትን መልካም ግን ያሳዩናል አልያም መጥፎውን ጎን ያስመለክቱናል። መጥፎው ሃሳብ ቢመራህ ነፍስህ ስትደክም፣ ስሜትህ ሲረበሽ፣ ውስጥህ ሰላም ሲያጣና ለእራስህ መሆን ሲያቅትህ ትመለከታለህ። መልካሙ ሃሳብ ሲመራህ ግን ነፍስህ ስታብብ፣ በእግዚአብሔር በረከት ስትታነፅ፣ ሰላምን ስታገኝ፣ ውስጥህ ሲረጋጋ፣ ደስታና ሃሴት ያንተ ሲሆኑ ታስተውላለህ።
አዎ! ጀግናዬ..! ማንን አስቀደምክ?
በማን እየተመራህ ነው? ለማን እራስህን አሳልፈህ ሰጥተሃል? ወደማን ተጠግተሃል? ማንንስ ከልብህ አምነህ ተከትለሃል? የምትከተለውን ብታውቅ ትርፉ ለእራስህ ነው። "የምጠፋው በማነው? የምለማውስ በማነው?" ብትል ከእራስህ ቀጥሎ የሚመጣው ነገር አብዝተህ የምትከተለው፣ አብዝተህ የምትመካበትና የተደገፍክበት ነገር ነው። ህልምህ ዋጋ ሲያስከፍልህ ትመለከታለህ ነገር ግን አታቆምም ምክንያቱም ውስጥህ ያለው የማያቋርጥ ሃሳብና እረፍት አልባ ምኞት እንድታቆም አያደርግህም። ስሜት አለህ፣ ፍላጎት አለህ፣ እቅድ አለህ፣ ግብ ይኖርሃል ነገር ግን በእያንዳንዱ ከመመራትህ በፊት ሚዛናዊነትን ማስቀደምና በብስለት መመራት ይኖርብሃል።
አዎ! ማንም እንድትከተው ቢመራህ በጭፍን አትከተለው፤ ማንም ሊያሳምንህ ቢጥር አስቀድመህ የእራስህን የግንዛቤ አቅም፣ የእራስህን የማስተዋል ደረጃ ለካ። መሪዎች ተመሪ እስካገኙ ድረስ ይመራሉ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በቀላሉ በተፅዕኗቸው ስር የሚወድቅ ቢያገኙ ይቆጣጠራሉ፣ ገዢዎች ደካማ አቅመቢስ ሃሳብን መሞገት፣ ሃሳብን መሰንዘር፣ አቋምን መግለፅ የማይችል ሰው ቢያገኙ በቀላሉ ይገዛሉ። የድጋፍህን ዋስትና በሚገባ ተረዳ፣ የያዝከው እንደሚያዋጣህ፣ የተማመንክበትም እንደሚታመን እርግጠኛ ሁን። ያመንከው እንዲቀድምልህ ትፈልጋለህ፣ የወደድከውም እንዲመራህ ትፈቅዳለህ። ፅንፍ በያዘ፣ ነፍስን በሚያረክስ፣ መንፈስን በሚያውክ፣ ጤናን በሚያናጋ ከፉ ሃሳብ አትመራ፣ ከሚነገርህና ከምታየው በላይ የእግዚአብሔርን ፍቃድ በመንገድህ አስቀድም፣ ጭንቅላትህን ሳይሆን ልብህን ለሚመራው ፈጣሪህ እራስህን ስጥ። የአምላክ ፀጋ ይበዛልህ ዘንድ ሃሳብህን ሁሉ ለአምላክህ የሚመች፣ ለሰውነትህም የተስማማ አድርገው።