ከባዱን ተሻገር!
፨፨፨//////፨፨፨
ተሰብሮ መኖር ከባድ ነው፤ ይቅርታ አለማድረግ ከባድ ነው፤ ስራ ማጣት ከባድ ነው፤ ወገን ማጣት፣ ረዳት ማጣት እጅግ ከባድ ነው። ነገሮች እንዳሰቡት ሳይሆኑ ሲቀሩ፣ እቅዶች አልሳካ ሲሉ፣ መንገዶች ሁሉ ምቾት ሲያጡ፣ ሸክሞች ሲበዙ፣ ጫናዎች ሲያይሉ ተስፋ አስቆራጭ ከባድ የህይወት ከስተቶች ከፊታችን ይደቀናሉ። ለአመታት የለፋንበት ትምህርት በቀናት ወይም በወራት ውስጥ ፍሬ አፍርቶ መመልከት እንፈልጋለን። ለረጅም ጊዜ አብሮን የነበረ ሰው በአንዴ ሲለየን በቅፅበት ልንረሳው እንሞክራለን፤ የፈተናዎችን እድሜ ማሳጠር፣ ችግራችንን ወዲያው መቅረፍ የሁልጊዜ ምኞታችን ነው።
አዎ! የደስታ ሰዓታት ቢረዝሙ፣ የፈተና ጊዜያት ቢያጥሩ መልካም ነበር። ነገር ግን ከባዱም ቀላሉም ነገር የእራሱ ቀነ ገደብና የተመጠነ ጊዜ አለው። ገፍተህ ወይም ሸውደህ የምታልፈው የፈተና ወቅት የለም፤ ይዘህ የምታቆየውም የደስታ ጊዜ አይኖርም። እጅጉን በብዙ ጥበቃህን የፈተነ፣ እንቅልፍህን ያሳጠህ ነገር ካለ የትኩረት አቅጣጫህን ቀይረው፤ እርሱ ካለሆነ ብለህ በጥበቃ ብዛት ሰውነትህን አታዝለው። ብዙ አሻጋሪ አማራጭ መንገዶች እንዳሉ ተመልከት። ቀጥተኛ መንገድ ባለሙያ አሽከርካሪ እንደማይፈጥር ሁሉ የተስተካከለና የተመቻቸ አካሄድም ሊያጠነክርህና ሊያሻሽልህ እደማይችል አስብ።
አዎ! ጀግናዬ..! ከባዱን ተሻገር! በፅናት ተፋለመው፤ በትግስት ተጋፈጠው፤ እራስህን አበርታ። ከባድ መሆኑን እንደማይታለፍ አትቁጠረው፤ አስቸጋሪ መሆኑ እንደማያልፍ አይሰማህ። የማያልፍ የለም፤ የማይረሳ፣ የማይዘነጋ ጊዜ አይኖርም። አስጨናቂ ሰዓታት ይረዝማሉ ምክንያቱም ሙሉ ትኩረታችን ጉዳዩ ላይ ስለሆነ፤ አስደሳች ጊዜያት ያጥራሉ ምክንያቱም ቅፅበቷን ከማጣጣም ይልቅ የማለቂያዋን ጊዜ ስለምንጠብቅ። አንተ ጋር የመጣ ሁሉ የሚታለፍ፣ የሚረሳ ነውና በቶሎ እጅ አትስጥ፤ ለመሰበር አትጣደፍ፤ ካንተ የቀረ ከሌለ አምላክህ የሚያስብልህን ጠብቅ፤ የእርሱ ምርጫ እንደሚስማማህ አትጠራጠር፤ በፅናትና ትዕግስትህም ተማመን።