ቆሻሻውን ተጠየፉ!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
ፀዴ ሁኑ፤ ንፅት ፅድት በሉ። የቆሸሸውን የጥላቻ አስተሳሰብ ተጠየፉ፣ ለጆሮ የሚጎረብጠውን የዘረኝነት አቋም ራቁት፣ ሰላም የማይሰጠውን የጎጠኝነትን አስተምህሮ ከአካባቢያችሁ አስወግዱ። አዕምሯችሁ በማይረባ የንቀትና የጥላቻ አመለካከት ተሞልቶ ከላይ ንፁህና ፅዱ ልብስ ብትለብሱ ምንም ዋጋ የለውም። አሁን አሁን በዚህ መንገድ የሚያምታቱ ሰዎች በዝተዋል። አለባበሳቸው ነጭ ነው አስተሳሰባቸው ግን ከጥላሸት የከፋ ጥቁር ነው፤ ሲታዩ ዘናጭ ይመስላሉ ንግግራቸው ግን እንደ ሬት ይመራል፣ ገፅታቸው በፈገግታ ተሞልቷል ቀርበው ሲታዩ ግን ውስጣቸው በክፋትና በጥላቻ ተተብትቧል፤ ከውጭ ለሚያያቸው ሀይማኖተኛ ጿሚ ፀላይ አስቀዳሽ ይመስላሉ ለቀረባቸው ግን ነውራቸው እጅግ የከፋ ነው። በጥሩ ልብስና ቁስ ሰውን ማታለል በጣም ቀላል ነው፣ ልብና ኩላሊትን የሚመረምረውን ፈጣሪ ግን መቼም ማታለል አይቻልም። ስለማንኛውም የሰው ልጅ ስለምታስቡት ሃሳብ ደጋግማችሁ ተመልከቱ፣ ስላለመመረዙና ስላለመቆሸሹ እርግጠኛ ሁኑ። የአስተሳሰባችሁ ጤንነት የህይወታችሁ ጤንነት ነው፤ የእያንዳንዱ አቋማችሁ ትክክለኝነት የስኬታችሁ ዋንኛ ምክንያት ነው። በቆሸሸ አመለካከት ላይ ቤት አትስሩ፣ በተመረዘ አካሔድ ወደፊት ለመጓዝ አትሞክሩ።
አዎ! ቆሻሻውን ተጠየፉ፣ መርዙን ወደ ህይወታችሁ አታስገቡ፣ በወደቀ አስተሳሰብ አትመሩ። ከምር ራሳችሁን የምታከብሩ ከሆነ ማንም በቂቤ የተለወሰ ምላስ ያለው ሰው የሚያቀብላችሁን የጥላቻ ሃሳብ አትቀበሉም፣ የእውነት የአዕምሮ ጤናችሁና የውስጥ ሰላማችሁ የሚያሳስባችሁ ከሆነ ቆሻሻውን መርዘኛ አስተምህሮ ለመጠየፍ ጊዜ አታጠፉም። ሀሳቡ አልሚም ይሁን አጥፊ፣ ጠቃሚም ይሁን ጎጂ፣ የጥላቻም ይሁን የፍቅር ማንኛውም ሰው የራሱ ሃሳብ አለው፣ ይህን ሀሳቡን የሚጭንበት ተቀባይም ይኖረዋል። ስንዴና እንክርዳዱን መለየት እየቻላችሁ፣ ዋናውን ሰብልና አረሙን እያወቃችሁ ማንም ራሱን እንደ አዋቂና ተመራማሪ ቆጥሮ የሚነዛውን አጥፊ አቋም እንደወረደ መቀበል አቁሙ። ሁሉም ሰው ነፃ ሃሳብ እንዳለው ሁሉ እናንተም ነፃ ሃሳብ አላችሁ፣ ሁሉም ሰው የመምረጥ አቅም እንዳለው እናንተም የሚበጃችሁን የመምረጥ አቅሙ አላችሁ። የትኛውም ስቃያችሁ የሚያበቃው እናንተ ልታስቆሙት ፍቃደኛ ስትሆኑ ብቻ ነው፤ ማንኛውም ሰው አስተሳሰቡን ሊጭንባችሁ የሚችለው እናንተ ስትቀበሉት ነው። ለይስሙላ አትኑሩ፣ ሰው ምን ይለኛል ብላችሁ ጠባብና አጥፊ አመለካከት ውስጥ አትዘፈቁ።
አዎ! ጀግናዬ..! የራስህ ሚዛናዊ አመለካከት ይኑርህ። ልክ እንዳየህ የምትፈርድ፣ የሰማሀውን ሁሉ የምታምን፣ ለጥሩውም ለመጥፎውም ጆሮህን የምትከፍት፣ ጠዋት ፅድቅ ቦታ ማታ ርካሽ ስፍራ የምትገኝ፣ እያወክ ወገንህን የሚያሸብር ዜና የምታሰራጭ ወይም የምትከታተል ሰው አትሁን። ከቆሻሻ ውስጥ ንፁህ ነገር አይወጣም፣ ከመጥፎ ተግባርም መልካም ውጤት አይገኝም። አውቀህና ፈልገህ እስካልገባህበት ድረስ ህሊናህ የእያንዳንዱን ነገር ትክክለኛነትና ስህተት መሆን በሚገባ ይነግርሃል። ጨላው በየት እንደሆነ፣ ብረሃኑም በየት እንደሆነ በሚገባ ይነግርሃል። ህሊናህን ማዳመጥ ያንተ ፋንታ ነው። ማሰብ እየቻልክ ከሚያስብ ሰው የማይጠበቅን የወረደ የጭፍን ጥላቻና የትምክህተኝነት አስተምህሮ የሚያስተላልፍ ሰው አትከተል። ተናጋሪ ሁሉ ትክክል አይደለም፤ ዝምተኛ ሁሉም ስህተት አይደለም። ማንም የፈለገውን ቢናገር ሰሚ አያጣም፣ ማንም ምንም ቢሰራ ተመልካች አያጣም። ምን እንደምትሰማ፣ ምን እንደምታይ በሚገባ አስበህ ወስን። ንፁ ሀሳብ እያለህ፣ ፅድት ያለ አቋም ኖሮህ የማንንም የቆሸሸና የረከሰ አስተሳሰብ ወደ ውስጥህ አታስገባ።