የቀረጥና ታክስ ሕጎች በቀላሉ የሚገኙበት የኦንላይን ድረ ገጽ ይፋ ሆነ
ታሕሳስ 2/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የኢትዮጵያ የቀረጥና ታክስ ሕጎች በቀላሉ የሚገኙበት የኦንላይን ድረ ገጽ ይፋ ሆኗል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር “ከሌክሲስ ኔክሲስ ሩል ኦፍ ሎው ፋዌንዴሽን” ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ድረ ገጽ÷ ከ300 በላይ የታክስ ሕጎች በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተቀመጡበት ነው ተብሏል።
በመርሐ ግብሩ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)÷ከዚህ በፊት የነበረው የታክስ እና ቀረፅ ሕጎች ለማህበረሰቡ ወይም ለግብር ከፋዩ የሚደርሱበት መንገድ አስቸጋሪና የተበታተነ እንደነበር ገልፀዋል።
ይህም ሀገሪቱ ከቀረፅና ታክስ ከምታገኘው ገቢ ላይ ጫና ፈጥሮ መቆየቱን ጠቅሰው÷ የኦንላይን ስርዓት መዘርጋቱ ዜጎች በቀላሉ ሕጎችን እንዲያገኙ በማድረግ የታክስ ስርዓቱን ግልፅና ፍትሃዊ ለማድረግ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ሥርዓቱ ገቢን በአግባቡ በመሠብሠብ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሕጎቹ በኦንላይን መቀመጣቸው የኢትዮጵያን የታክስና ቀረጥ ሕጎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል ነው ብለዋል።
ይህም ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ የታክስ ሕጎችን በቀላሉ ማወቅ እንደሚያስችላቸው ተጠቁሟል፡፡
የታክስ እና ቀረጥ ሕጎችን https://ethiopia.mylexisnexis.co.za/#/navigation-view;listCode=LNSA ላይ ማግኘት እንደሚቻል ተመላክቷል።