በበጀት ዓመቱ የአምስት ወራት የገቢ አፈፃፀም እና የቀጣይ ወራት ዕቅድ ዙሪያ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል
ታሕሳስ 5/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስቴር በ2017 በጀት ዓመት የአምስት ወራት የገቢ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በታዩ ክፍተቶች እና ጠንካራ ጎኖች ላይ ውይይት ይደረግበታል፡፡
በዚሁ መድረክ የቀጣይ ወራት የሥራ ዕቅድ ቀርቦ በአተገባበሩ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ይካሄድበታል፡፡
በተጨማረም ተቋማዊ ውጤታማነትን እንዲሁም ተወዳዳሪነትን ማረጋገጠ እንዲቻል በተዘጋጀው የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ላይ የሥራ ክፍሎች በአጭር ጊዜ ማከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
መድረኩ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በመድረኩም የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ፣ የታክስ ሥርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ መስከረም ደበበ፣ የተቋማዊ አቅም እና ድጋፍ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ኡሚ አባጀማል እንዲሆም የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጆች ፣ ምክትል ስራ አስኪያጆች፣ ዳይሬክተሮች፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተቋማዊ አቅም እና ድጋፍ ዘርፍ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በተክሉ ኤልያስ
ፎቶ፡- የትናየት እንዳያፍሩ