በQR Cod የተደገፈ የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት የህትመት ጥያቄያቸውን ማቀረብ እንደሚገባቸው ተገለፀ
የካቲት 24/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
በገቢዎች ሚኒስቴር የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ካሣሁን ደመመ ሀሰተኛ ደረሰኝ የገቢ አሰባሰብ ተግባር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር የቆየ መሆኑን እና ግብር ከፋዩን ባለተገባ መልኩ ለታክስ ማጭበርበር ወንጀል ሲዳርግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመቅረፍም የደረሰኝ አስተዳደር እና አጠቃቀም ሥርዓትን በማሻሻል በQR Cod የተደገፈ እና ሚስጥራዊ መለያ ያካተተ የደረሰኝ ህትመት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኑ በግብር አሰባሰቡ ላይ በጎ ውጤት እንደሚያመጣ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
እንደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በርካታ ችግሮች እያጋጠሙ የነበረ መሆኑን እና በተያዘው በጀት ዓመትም በሀሰተኛ ደረሰኝ ምክንያት በ5 ድርጅቶች አለአግባብ ሊቀናነስ የነበረ 104 ሚሊየን ብር ገቢ በኦዲት ሥራ አማካኝነት ማዳን መቻሉን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ አዲሱ የደረሰኝ ህትመት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/b6O90