#ከዜናዎቻችን| የብልፅግና መንግስትን በመተቸት የሚታወቁት ግለሰብ የደህንነት ሀላፊው አማካሪ ሆነው ተሾሙ
(መሠረት ሚድያ)- መንግስትን በመተቸት የሚታወቁት የፖለቲካ ተንታኙ እና የቀድሞው የዛሚ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣብያ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ተሾመ የመንግስት ሹመት እንዳገኙ መሠረት ሚድያ አረጋግጧል።
አቶ ዘሪሁን የደህንነት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት የአቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ ሆነው ከጥቂት ወራት በፊት ሹመት እንደተሰጣቸው ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
የዛሬ ሰባት አመት ገደማ የአሁኑ መንግስት ስልጣን በያዘበት ወቅት የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁት እና የጋዜጠኛ ሚሚ ስብሀቱ ባለቤት የሆኑት አቶ ዘሪሁን ለቀድሞው የኢህአዴግ ባለስልጣናት እና ለስርዐቱ አራማጆች እጅግ ቅርብ እንደነበሩ ብዙዎች ይናገራሉ።
ለውጥ መጣ የተባለበትን ወቅት "የጎበዝ አለቆች ወጥቶ መግባትን ከባድ ያደረጉበት ግዜ ነው" በማለት በመተቸት የሚታወቁት ግለሰቡ ወቅቱ መደማመጥ የሌለበት ስለሆነ በጥሞና ዝም ለማለት በመፈለጋቸው ከሚድያ እይታ ርቀው እንደነበር ተናግሮ ነበር። ዛሚ ኤፍ ኤም ከተዘጋ በኋላም አብዛኛ ግዜያቸውን በአሜሪካ እንዳሳለፉ ታውቋል።
አሁን ግን በአዲስ ሹመት መንግስትን የተቀላቀሉ ቢሆንም እስከዛሬ ድረስ ሹመቱ በመንግስት ይፋ አልሆነም፣ ይሁንና ከሶስት ቀን በፊት በዋልታ ሚድያ ላይ ቀርበው ስለ ወቅታዊው የሶማልያ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ውጥረት ትንታኔ ሲሰጡ እንደነበር ተመልክተናል።
(#ከዜናዎቻችን በሳምንቱ በቪድዮ ዩትዩብ ላይ ያቀረብናቸውን የተመረጡ መረጃዎች ቆየት ብለን በድጋሜ በፅሁፍ የምናቀርብበት አምድ ነው)
መረጃን ከመሠረት!