ግብፅ እና ኤርትራ የሶማሊያን ሉዋላዊነት ለማክበርና የሀገሪቷን ጦር ለማጠናከር ተስማምተናል አሉ‼️
ግብፅ እና ኤርትራ የሶስትዮሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ ኤል ሲሲ፣ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድን ጨምሮ ለሶማሊያ ማንኛውንም አይነት ድጋፍ ለመስጠት መስማማታቸውን ሃሙስ እለት አስታውቀዋል።
የኤርትራ፣ ግብጽና ሱማሊያ መሪዎች ትናንት አሥመራ ላይ ባደረጉት ስብሰባ፣ የጋራ ትብብራቸውን ለማጠናከር በውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቻቸው ደረጃ የሦስትዮሽ የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም ወስነዋል።
መሪዎቹ፣ የሱማሊያ መንግሥት ተቋማት የውስጥና የውጭ አደጋዎችን መመከት እንዲችሉ ድጋፍ ለማድረግም ተስማምተዋል።
አገራቱ፣ የቀጠናው አገራትን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ለማክበር ከስምምነት መድረሳቸውንም ገልጸዋል።
የኤርትራ እና ግብፅ መሪዎች በሶማሊያ መረጋጋትን ለመደገፍ እና የፌደራል መንግስቷን አቅም ለማጠናከር የሚያደርጉትን ጥረት በደስታ ተቀብለዋል።
በተጨማሪም ግብፅ በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር በሚደረገው ጥረት ኃይሏን ለማበርከት ያቀረበችውን ጥያቄ አወድሰዋል።
=============🎉🎉🎉
Via Ayu zehabesha