"መንግሰት ከታጣቂ ሃይሎች ጋር ያለውን ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት ለህዝቡ ግልጽ ማድረግ አለበት"- ኢዜማ‼️
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ ) ባወጣው መግለጫ በሰላም ስምምነቱ መሰረት እየገቡ ካሉ ታጣቂ ሀይሎች ጋር ያለውን ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት መንግስት ለህዝቡ ግልጽ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡
ኢዜማ በመግለጫው አክሎም "ወደ ከተማም ሆነ ወደ ተሐድሶ ሥልጠና የሚገባ ታጣቂ ኃይል በሙሉ ትጥቁን ሙሉ ለሙሉ ለሚመለከተው የጸጥታ አካል አስረክቦ መሆን አለበት" ብሏል::
በመሆኑም በተለያዩ ቦታዎች ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ የጥይት ተኩስ ማድረጋቸው ንፁሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እና የስነ ልቦና ጫና የሚያሳድር፤ አግባብነት የሌለውም ተግባር መሆኑ ታውቆ በሁሉም ቦታዎች ላይ እንዲቆም አሳስቧል፡፡
ይህን ተከትሎም ትናንት ምሽት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የተሰማውን ተኩስ ተከትሎ ለዜጎች ድንጋጤ እና መረበሽ ይቅርታ ቢጠይቅም ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት የንጹሀን ዜጎች ህይወት ማለፉ እየተነገረ መሆኑን ፓርታው ጠቁሟል፡፡
"ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ሕግና ሥርዓትን በማክበር መሆኑ መዘንጋት አይኖርበትም" ሲልም አሳስቧል።