ጃዋር ስለ አንካራው ስምምነት በፌስቡክ የፃፈው 👇
- ከሶማሊላንድ ጋር ተደርጎ የነበረው ስምምነት ኢትዮጵያ ሶማሌላንድን እንደ ነጻ ሀገር እውቆና ለመስጠት፤ በምትኩም ለወደብ እና የባህር ኃይል የሚሆን የባህር በር ማግኘት እንደነበር የሚታወስ ነው። የአንካራው ስምምነት ደግሞ ኢትዮጲያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር፣ ሶማሊያ ደግሞ ወደቦቿን ኢትዮጲያ እንድትጠቀም እንድትፈቅድ የሚል ነው።
- ይህ ማለት የአንካራው ስምምነት ኢትዮጲያን የባህር ወደብ ባለቤትነት ሳይሆን የመጠቀም መብትን የሚወስን ነው። ማለትም የኢትዮጲያ መንግስት በሶማሊላንዱ ስምምነት ተጎነጻፍኩት ሲለው የነበረው የወደብ ባለቤትነት ቀርቶ፣ የሶማሊያንም ሆነ የሌላ ሀገራትን ወደብ በሊዝ፣ በኮንትራት ወዘት የሁለትዮሽ ስምምነት መጠቀም ትችላለች በሚለዉ ተተክቷል። ይህ ደግሞ እንደ United Nations Convention on the Law of the Sea (UNCLOS) ያሉ የአለም አቀፍ ህጎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ሶማሊያም ሆነች ሌሎች ጎረቤቶቻችን ድሮውንም የተቀበሉት ጉዳይ ነው።ለምሳሌ ጂቡቲ የታጁራን በሊዝ ለኢትዮጲያ ለመስጠት እንደምትፈልግ ደጋግማ ተናግራለች።
ሲጠቃለል የአንካራው ስምምነት የኢትዮጲያ እና ሶማሊያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲሁም ኢትዮጲያ የወደብ ባለቤት ለመሆን የምታደርገውን ሙከራ ከአምና (የሶማሊልንዱ ስምምነት ከተፈረመበት ከጃኑዋሪ 1፣ 2024) በፊት ወደነበረበት የሚመልስ ነው። ለዚሁ ነበር ያን ሁሉ ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ የተከፈለው?
ሀገር የምትመራው በእውቀት ላይ በተመሰረተ የሰከነ እቅድ ይልቅ በባብዶ ምኞት ሲሆን ውጤቱ ሀገራዊ ተዓማኒነት (credibility) በእጅጉ መጉዳት ነው።