ዜና: “#የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እስከ ሚቀጥለው ምርጫ ድረስ የስልጣን ግዜ እንደሚኖረው ጠ/ሚኒስትር አብይ አስታወቁ
በትግራይ ክልል በቀጣይ እንደ አዲስ የጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚቋቋም ጠ/ሚኒስትር #አብይ አህመድ (ዶ/ር) አመላከቱ፤ በአዲስ መልክ የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደሩ “እስከሚቀጥለው ምርጫ ድረስ ስራውን እየሰራ ህዝቡን ለምርጫ ማዘጋጀት እና ህዝቡን የስልጣን ባለቤት የማድረጉን ሂደት ማረጋገጥ ይጠበቅበታል” ብለዋል።
በቀጣይ የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተጨማሪ የህግ ማሻሻሎች ተደርገውበት ይመሰረታል ብለዋል፤ “ህግ ሲሻሻለ ደግሞ እስካሁን የነበረው አፈጻጸመ መገምገም አለበት” ሲሉ የተደመጡት ጠ/ሚኒስትሩ “ተገምግሞ መጠነኛ ለውጥ ተደርጎ የፕሪቶርያን ስምምነት በሚያከብር መንገድ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እስከሚቀጥለው ምርጫ ድረስ ስራውን እየሰራ ህዝቡን ለምርጫ ማዘጋጀት እና ህዝቡን የስልጣን ባለቤት የማድረጉን ሂደት ማረጋገጥ ይጠበቅበታል” ሲሉ ገልጸዋል።
ባለፉት ሁለት አመታት በፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ እና በምክትሎቻቸው ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ የተመራው አስተዳደር ሁለት አመት ጦርነት እንዳይፈጠር፣ ሁለት አመት ያሉ ጥያቄዎች በንግግር እንዲመለሱ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል” ሲሉ አወድሰዋል።
“ምንም እንኳ ቀድሞ በተካሄደው ውጊያ ብንወቅሳቸውም፣ ላለፉት ሁለት አመታት ለሰሩት ስራ ግን ማድነቅ ማመስገን እንፈልጋለን። ተጨማሪ ውጊያ እንዳይነሳ ሙከራ አድርገዋል” ብለዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7286