Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
" መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ ይገኛል " - ባለስልጣናት
በአሜሪካ ፤ ሎስ አንጀለስ የተነሳው ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር ያልተቻለ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ወደ 24 ከፍ ብሏል። 16 ሰዎች ደግሞ የገቡበት አይታወቅም።
በሎስ አንጀለስ ዙሪያ 3 አካባቢዎች መቃጠላቸውን ቀጥለዋል።
በአሁኑ ላይ ትልቁ እሣት ሚገኘው በፓሊሳድስ ሲሆን 9307 ሔክታር መሬትን ሲያቃጥል 11 በመቶውን መቆጣጠር ተችሏል።
የኢቶን እሳት በትልቅነቱ 2ኛ ደረጃ ሲይዝ ከ5665 ሔክታር በላይ አቃጥሏል። 27 በመቶው በቁጥጥር ስር ውሏል።
ከሞላ ጎደል በቁጥጥር ስር በዋለው በሃረስት እሳት 323 ሄክታር መሬት መቃጠሉ ታውቋል።
የእሳት አደጋ ሠራተኞች ትልቁን እሳት መቆጣጠር ቢጀምሩም ባለስልጣናት ግን ቀጣዮቹ ንፋሶች " አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የንፋስ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ ይገኛል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
እሳቱ በአሜሪካ ታሪክ አውዳሚው ለመሆን መቃረቡ ተገልጿል።
የግል ትንበያ ተቋም የሆነው " አኩዌዘር " በእሳት ቃጠሎ የተነሳ የደረሰው ኪሳራ ግምት ከ250 እስከ 275 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል።
ለሌላ በኩል ፥ የአደጋ ቀጠና ከሆኑ ቦታዎች ሰዎች እንዲወጡ የታዘዘ ሲሆን የወጡም አሉ።
ነዋሪዎች እንዲወጡ በታዘዙባቸው አካባቢዎች ዝርፊያ ሲፈፅሙ የነበሩ 29 ሰዎች መታሰራቸው ተነግሯል።
ሰዎች ቤታቸው ለቀው ሲወጡ ሲዘርፉ የነበሩ በርካቶች ነበሩ።
ከዚህ ባለፈ ፥ በሰደድ እሳቱን ምክንያት አከራዮች በህገወጥ መንገድ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጭማሬ ማድረጋቸው ተነግሯል።
እሳቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ይጠየቅበት ከነበረው የቤት ኪራይ በሺዎች በመጨመር እንደተጠየቁ አንዳንዶች ገልጸዋል።
በሰደድ እሳቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸው አመድ ሆኗል። በርካታ የተፈናቀሉ ተጎጂዎች " የማይቀምስ የቤት ኪራይ እና የሆቴል ክፍያ እየተጠየቅን ነው " ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
©: ቲክቫህ ኢትዮጵያ