የደብዳቤው ትርጉም‼
================
«የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው የመማር ክልከላ ታገደ
~~~~~
ሰሞኑን የበርካታ መገናኛ ብዙሃን፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ የሀይማኖት ተቃማት፣ አግባብ ያላቸው አካላትና ግለሰቦች አጀንዳ የነበረው በአክሱም የሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ጉዳይ በፍርድ ቤት ጊዜያዊ ውሳኔ አግኝቷል።
በአክሱም ከተማ የሚገኙ አምስት ትምህርት ቤቶችና የከተማዋ ትምህርት ጽ/ቤት የሙስሊም ተማሪዎችን ህጋዊ፣ ሰብአዊና ሀይማኖታዊ መብት በመጣስ ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ ከልክለው እንደነበር ይታወሳል።
ክልከለውን በመቃወም በተለያዩ መንገዶች ሲቀርብ ለነበረው ጥያቄና ተቃውሞ የትምህርት ቤቶቹና የትምህርት ጽ/ቤቱ ኃላፊዎች አዎንታዊ ምላሽ ባለመስጠታቸው ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ ነበር።
በመሆኑም በትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የክስ አቤቱታ ቀርቦለት የነበረው የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በዝርዝር ተመልክቶ ዛሬ ጊዜያዊ ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህም መሰረት የክስ ክርክሩ ውሳኔ እስኪሰጥ ክልክላው ቢዘልቅ በተማሪዎቹ ላይ የማይቀለበስ የመብት ጥሰት ሊያስከትል እንደሚችል የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ ተማሪዎቹን ለማገድ የተላለፈው አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲታገድ አዟል።
እግዱ የክስ ሂደቱ ውሳኔ እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥ ድረስ እንደሚፀና የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ ተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው የመማር መብታቸው እንዲከበር እና በክልከላው ምክንያት የምዝገባ ጊዜ አልፏቸው የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በነገው እለት በልዩ ሁኔታ እንዲመዘገቡ ወስኗል::
ለተፈጻሚነቱም ክልከላውን ለፈጸሙት ትምህርት ቤቶች በአድራሻ የፍርድ ቤቱ የእግድ ውሳኔ እንዲደርሳቸው ተደርጓል::
በተጨማሪም ተከሳሾች የፊታችን ጥር 16/2017 በአካል ችሎት ተገኝተው በቃል ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዟል::»
Hanan እንደተረጎመችው።