ማኅበራዊ ሚድያን በመጠቀም በግለሰቦችና በቡድኖች እየተፈጠረ ያለውን ሃይማኖት ለበስ ችግር መንግሥት የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል ባወጣው ሕግ መሠረት ሕግን የማሰከበርና ተጠያቂነት እንዲያሰፍን የማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን።
ችግሩ የማኅበረሰብ የጸጥታ እና የሰላም ዕጦት ፈተና ከመሆኑ በፊት የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ለችግሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት እና ተገቢውን ክትትል በማድረግ መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን።
ንጽጽራዊ ትምህርተ ሃይማኖት ወይም ዕቅበተ እምነታዊ ሥራዎች ለማኅበረሰቡ አስተማሪ በሆነ መልክ በሃይማኖት ሊቃውንቶች መካከል የሚደረግ፣ በሥርዓትና በመከባበር የሚከወን እና ስክነትና ሥነ-ስረዓት የሚጠይቅ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።
ይሁንና ማህበራዊ ሚድያን በመጠቀም ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ሆነ ንጽጽራዊ ትምህርቶችን የሚያቀርቡ ወገኖች እነዚህን መርሆዎች ባከበረ መልኩ እንዲያከናወኑና ለትውልዱ አርኣያ በመሆን ለዘመናት በህዝባችን መካከል የቆየውን አብሮነትና ወንድማማችነትን በማይጎዳ መልኩ እንዲተገብሩ አባታዊ ምክራችንን እናስተላልፋለን፡፡
እንደሚታወቀው ጊዜው በክርስትና እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ወርኃ ጾም በመሆኑ ለሀገራችን እና ሕዝባችን የፈጣሪን ቸርነትና ምህረት እዝነት የምንለምንበት የተለየ ጊዜ ነው፡፡
በዚህ የጾም ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ችግር መፈጠሩ አሳዛኝ ቢሆንም፥ በሌላ መልኩ እየተፈጠረ ያለውን ይህንን አሳሳቢ ጉዳይ ወደ ፈጣሪ ለማቅረብ ዕድል የሰጠ በመሆኑ መላው የከተማችን የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮች በጽሞና እና በትህትና ወደ ፈጣሪ በመቅረብ ፈጣሪ ለሃገራችን ጽኑ ሰላምን እንዲሰጥልን ልንማጸን ይገባል ሲል ጉባኤው ለሀሩን ሚድያ በላከው የአቋም መግለጫ አስታውቋል።
©ሀሩን ሚድያ