የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) ከኖርዲክ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ተቀማጭ ከሆኑ የኖርዲክ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮችን በዳሰሰው ውይይት የኖርዌይ፣ ስዊድን እና ፊንላንድ አምባሳደሮች ተገኝተዋል።
በውይይቱ ኢትዮጵያ ከኖርዲክ ሀገራት ጋር ረጅም ዓመታት የዘለቀ የፓለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዳላት ያነሱት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ፤ ይህንንም አጠናክራ ለመቀጠል እየሰራች ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በፓለቲካ እና ኢኮኖሚ መስክ እየተተገበሩ ስለሚገኙ የለውጥ ስራዎች ገለጻ ያደረጉት ሚኒስትሩ፤ ለውጭ ባለሐብቶች እየተፈጠረ ያለው ምቹ ሁኔታን ተጠቅመው የኖርዲክ ሀገራት ኩባንያዎች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የብሔራዊ ምክክር ሂደቱን በአብነት አንስተው ገለፃ አድርገዋል።