የሶማሊያዉ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ አዲስአበባ ገቡ!
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ ለይፋዊ ጉብኝት ዛሬ አመሻሹ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል። የፕሬዝዳንት ሞሐመድ ጽሕፈት ቤት፣ የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት በኹለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነትና የጋራ ዓላማዎችን ለማጠናከር ያለመ እንደኾነ አስታውቋል። ዐቢይና ፕሬዝዳንት ሞሐመድ የአንካራውን የባሕር በር ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ በአካል ሲገናኙ የዛሬው የመጀመሪያቸው ነው። ፕሬዝዳንቱ ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት፣ ካምፓላ ላይ ዛሬ በተካሄደው የአፍሪካ "ኹሉን ዓቀፍ የግብርና ልማት" አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ በኋላ ነው። በካምፓላው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ናቸው።