“ ህዝቡ በመረጣችሁት መንገድ ይታገላችኋል “ - በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት
በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ፤ ትናንት ጥር 15/2017 ዓ.ም “ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን “ በሚል የተሰጠውን መግለጫ የሚቃወም መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም መግለጫው ፥ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት” የነሃሴው “ ብሎ ሲጠራው ራሱን ደግሞ “ ነባር “ በማለት ገልጿል።
“ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን “ በሚል ያወጡት መግለጫ የ “ ነሃሴው ህወሓት ህዝቡን እና ሰራዊቱ ለመበታተነ የሰራው ክፋት ውጤት ነው “ በማለት ገልፆታል።
“ የነሃሴው ህወሓት ህዝብን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያልተቀበለው ጉባኤ በማካሄድ ነባሩን ህወሓት እንዲዳከም ሰርቷል “ ሲል በአቶ ጌታቸው የሚመራው ህወሓት ፤ “ ወታደራዊ አምባገንነት ታግሎ ዴሞክራሲያዊ እና ህዝባዊ መንግስት የጨበጠ ህዝብ ወደ ኋላ አይመለስም “ ብሏል።
“ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን “ በሚል ስም የወጣውን መግለጫ “ የጦርነት አዋጅ ነው ፤ በህዝብ ላይ አፋኝ አስተዳደር የሚጭን ተቀባይነት የሌለውና የውድቀት ጥሪ “ ሲል ገልጾታል።
“ ህዝቡ በመረጣችሁት መንገድ ይታገላቹሃል “ ያለው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት “ የጦርነት አዋጃችሁ የፕሪቶሪያ ስምምነት አፍርሶ ፤ ትግራይ ለአህጉራዊ ዓለምአቀፋዊ ተነጥሎ እና ውግዘት የሚዳርግ ህዝቡን ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው “ ሲል አክሏል።
የአነ አቶ ጌታቸው ቡድን መግለጫውን መላ የትግራይ ኃይል አባላት እንዲያወግዙት ጠይቆ “ ህዝብን እና መንግስታችሁ በሚስጡዋችሁ አቅጣጫ ብቻ እንድትንቀሳቀሱ ጥሪያችን እናቀርባለን “ ሲል አሳስቧል።
ህዝቡ እና ወጣቱ በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ገልጾ ይህንኑ በመገንዘብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትግሉ በማጠናከር ለመብቱ ለአንድነቱ እና ለህልውናው በመታገል የተደቀነበት አደጋ እንዲመከት ጥሪ አቅርቧል።
ለህዝቡ ፣ ለዳያስፓራ ፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት “ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን “ በሚል ስም የወጣው መግለጫ እንዲያወግዙት ጠይቀዋል።
መግለጫውን ያወጡት አመራሮች ያለፈ ታሪካቸው ከሚያጎድፍ ተግባር በመውጣት አሁን የፈፀሙት ስህተት በአስቸኳይ እንዲያርሙ እና ታሪካቸው እንዲያድሱ ጥሪ አቅርቧል።