ግንቦት 20 ከአሁን በኋላ አይከበርም - የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።
አዋጁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት ሲሆን፤ ክልሎች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ህግ አውጥተው በክልል ደረጃ የሚከበሩ አዋጆችን አከባበር መወሰን ይችላሉ ተብሏል።
ይህ የሚመለከተው እንደ ኢሬቻ፣ ጊፋታ፣ ጨምባላላ፣ አሸንዳ ፣ ሻደይ ፣ አሸንድዬ ፣ ...ሌሎችንም ሲሆን ክልሎች በራሳቸው አዋጆችን አውጥተው አከባበሩን መወሰን እንደሚችሉ ተመላክቷል።
➡️ በልማድ ሲከበር የቆየውን “ ግንቦት 20 “ ብሔራዊ በዓልነቱ #አስቀርቷል፡፡
➡️ የሰማዕታትን ቀን ( #የካቲት_12 ) እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ( #ህዳር_29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ #ታስበው ይውላሉ።
➡️ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ፣ የሰንደቀ አላማ ቀን ፣ የሴቶች ቀን ፣ የአፍሪካ ቀን ሌሎችም ታስበው ይውላሉ።
➡️ የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ይከበራል።
➡️ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ ያለባቸው ተቋማት ዝርዝር ተቀምጧል።
በዚህም ፦
° የውሃ
° የመብራት
° የስልክ
° ሚዲያዎች (ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ)
° የጤና ተቋማት እና መድሃኒት ቤቶች
° መከላከያ
° ፖሊስ
° ደህንነት
° የእሳት አደጋ መከላከል
° የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች
° ነዳጅ ማደያዎች
° ሙዝየሞች ፣
° ፓርኮች ክፍት ሆነው ከሚውሉት ውስጥ ናቸው።