በተለምዶ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዉሏል‼️
በዛሬው ዕለት በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ከቀኑ 6 ሰዓት ከ35 ላይ በመኖሪያ ቤቶች ላይ አጋጥሞ የነበረዉ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።
በአደጋዉ ቆሮቆር በቆርቆሮ ሆነዉ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎችና ሁለት የውሀ ቦቴዎች ከ70 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርተው ነበር።
የእሳት አደጋዉ በአካባቢዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶችና ተቋማት እንደዚሁም በአቅራቢያዉ ባለ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንዳይዛመት ማድረግ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የአደጋዉ መንስኤና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን እየተጣራ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ጉዳት አለመድረሱን ኮሚሽኑ ጠቁሟል። አሁን ያለንበት የጥቅምት ወር ደረቅና ነፋሻማ አየር ያለዉ በመሆኑ ለእሳት አደጋ መከሰትና መባባስ አስተዋጾኦ ስለሚያደርግ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል።