"ጽንፈኛው ቡድን በፈረስ ቤት 37 ወገኖችን በግፍ ጨፍጭፏል" አቶ ደሳለኝ ጣሰው
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የክልሉ የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል። ማኅበረሰቡ ለሰላም ያለው ግንዛቤ ትልቅ ነው ያሉት ኀላፊው ለሰላም የሚከፍለው ዋጋ ከፍ ያለ መኾኑንም ገልጸዋል።
ከሕግ ማስከበር ጎን ለጎን ለሰላም የሚዘጋ በር የለም በሚል ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ሲቀርቡ መቆየታቸውንም አመላክተዋል። መንግሥት በድርድሩ ብቻ ውጤት ይገኛል ብሎ ባይቀመጥም የሰላም አማራጮች ግን አሁንም ዝጎች አይደሉም ነው ያሉት። ማኅበረሰቡ መንግሥት ለሰላም ለሰጠው አማራጭ ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል።
ነፍጥ ባነሳ ኃይል ላይ ሕግ ማስከበር ግድ መኾኑንም ገልጸዋል። እስካሁን በተሠራው ሥራ 2 ሺህ 594 ታጣቂዎች ሲያደርጉት የነበረው ድርጊት ተገቢ አለመኾኑን ተረድተው ለሰላም መግባታቸውን ተናግረዋል። በየቀኑ ለሰላም የሚገቡ ታጣቂዎች መኖራቸውንም አስታውቀዋል።
ጽንፈኛው ቡድን በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ሚካኤል በሚባል ሥፍራ የሕዝብ እና የመንግሥት አገልግሎት የሚሰጡ 97 የኅብረተሰብ ክፍሎችን ከመስከረም 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ አሥሮ መቆየቱን ጠቁመዋል። ከቤተሰቦቻቸው ከመቶ ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ እየተቀበለ ቆይቶ ዛሬ ኅዳር 27/2017 ዓ.ም 37 ወገኖችን በግፍ ጨፍጭፏል ነው ያሉት።
ጽንፈኛው ቡድን የፈጸመው ድርጊት አሳዛኝ እና ዘግናኝ መኾኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው እንኳን ወገናቸውን ሀገራቸውን ሊደፍር የመጣን ጠላት እንኳን ሲማርኩ ተንከባክበው፣ ድርጊቱ ልክ እንዳልኾነ አስተምረው የሚልኩ ናቸው ያሉት ኀላፊው ጽንፈኛው ቡድን ግን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ስብዕና ባፈነገጠ መልኩ የራሱን ወገኖች በግፍ ይገድላል ነው ያሉት።
ጽንፈኞች የያዛዟቸውን ወገኖች እጅ እና እግራቸውን እያሠሩ ሁለት ወራት ካቆዩ በኋላ በግፍ መግደላቸውን ነው የተናገሩት። የቀሩት ወገኖችንም በግፍ ሊገድሏቸው እንደሚችሉም ገልጸዋል። ከዚህ በፊትም በተናጠል የሚረሽኗቸው ወገኖች በርካቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።
ሕዝቡ በጽንፈኞች ምክንያት በራሱ ከተማ፣ ክልል እና ሀገር እንዳያለማ፣ እንዳይነግድ እና እንዳይኖር ኾኗል ነው ያሉት። ሕዝቡን ከግፍ ቀንበር ለማውጣት እየተወሰደው ያለውን እርምጃ ሕዝቡ እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል።
በፈረስ ቤት ሚካኤል በጽንፈኛው ቡድን በተፈጸመው አሰቃቂ ግፍ የክልሉ መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልጻል ነው ያሉት። የተፈጸመው ድርጊት ከአማራ ሕዝብ ታሪክ ያፈነገጠ እና ነውር መኾኑንም ነው የተናገሩት። መንግሥት ይህን ድርጊት በፈጸመው የጽንፈኛ ቡድን ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።