ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ።
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በአምስት አመቱ ተቋማዊ ሪፎርምና በውጪ ጉዳዮች ሰላምና ደህንነት ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።
ከተቋማዊ ለውጡ በመነሳት ተቋሙ ከለውጡ በፊት የነበረበትን ከፍተኛ የሆነ ችግር በመቅረፍ ሠራዊቱን ከሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች ተዋፅኦ እንዲኖረው በማድረግ፣ ሃገራችንን በሚመጥን መልኩ እንደ ኢትዮጵያ እንዲያስብ ተደርጎ እየተገነባ ያለ መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገልፀዋል።
በአዲሱ ስትራቴጂ ከለውጡ በፊት የነበሩትን መመሪያዎች በመፈተሽ እና እንደ አሥፈላጊነቱ በመቀየር የሠራዊቱን ኑሮና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች በማሻሻል፣ ሠራዊቱ ከየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት ከሃይማኖትና ከብሄርተኝነት ነፃ የሆነ አስተሳሰብ እንዲኖው የማድረግ ሥራ መሠራቱን አንስተዋል። አየር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና ምድር ሃይልን በማጠናከር ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ሠራዊቱን መገንባት መቻሉንም አሥረድተዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፀረ ሰላም ሃይሎች ሠላም መርጠው በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ እየተሰራ ያለ መሆኑን ጠቅሰው ሠራዊቱ ልምድ ያለው በመሆኑ ከሀገርም አልፎ በቀጠናው አገራት እንዲከበር አድርጎታል ነው ያሉት።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትም ሰፋ ያሉ ጉዳዩች ላይ ሃሳብ አንስተው የተወያዩ ሲሆን አጠቃላይ ስለተደረገላቸው አቀባበልና ሠፊ ገለፃ ምስጋና አቅርበዋል።