“ የባህር በር ጥያቄን ማንሳት ነውርነቱ አቁሟል “ - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ስትል ኤርትራን የመውረር ፍላጎት እንደሌላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
“ የኢትዮጵያ ፍላጎት እንነጋገር፣ ሰጥቶ በመቀበል መርህ፣ ህዝቦች በሚጠቀሙበት መርህ እንወያይ የሚል ነው “ ብለዋል።
“ የኤርትራ ህዝብ የሚያስፈልገው ልማት ነው፣ ተባብረን መልማትና መስራት እንጂ አንዱ አንዱን መውጋት የእኛ እቅድ አይደለም “ ነው ያሉት፡፡
“ ኢትዮጵያ ላይ ማንም ሀገር ወረራ ሊፈጽም እና ከጀመርነው ህልም ሊያስቆመን ይችላል የሚል ስጋት የለብንም “ ብለዋል፡፡
“ በቂ ዝግጅት ስላለን ማንም አያስቆመንም፣ ዝግጅት የምናደርገውም ጦርነትን ለማስቆም ነው “ ሲሉ አክለዋል፡፡
“ የባህር በር ጥያቄን ማንሳት ነውርነቱ አቁሟል “ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አቋምም በዓለም ላይ ትልቅ ሀገር ሆኖ የባህር በር የሌለው የለም ስለሆነም በሰጥቶ መቀበል መርህ ሊሆን ይገባል የሚል ነው “ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
“ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ አጀንዳ ለመስጠት የመጣ ሳይሆን ባለፉት ዓመታት ትኩረት የተሰጠው እና በመደመር መጽሐፍ ላይ የተካተተም ነው “ ብለዋል፡፡