+ ደስታችን ሆነ +
እግዚአብሔር "ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ "ዘፍ 3-22 በማለት አዳምን እርሱ ሰው ሲሆን ሰውን አምላክ በማድረግ የመሆን መሻቱን በሰው ስጋ ተገልጦ(ተወልዶ) እንደሚፈጸምለት የተሰፍ ቃል ገብቶለታል ቅዱስ ያሬድ በድጓ ሲገልጥ ፦ "ወይቤሎ ለአቡነ አዳም እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርሕብከ ወእከውን ሕፃነ በእንቲአከ ፤ አባታችን አዳምን እንዲህ አለሁ"ከልጅ ልጅህ እወለዳለሁ ፣ በአደባባይህም ዳዴ እላለሁ ስለ አንተም ሕፃንን እሆናለሁ " ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ ደግሞ ፦ አዳም ወዴት አለኽ ? ምናልባት አትብላ ያለኩኽን በላኽን የሚሉት ቃላት ጥያቄ አዳም አንተ ኹሉን ቻይ ንጹሕ ባሕርይ እኔን መኾን አትችልም እንጂ ሠሪ ከሠራው ቤት ሊገባ ችሎታ እንደ አለው እንዲሁ እኔም አንተን መኾን እችላሉሁ እንደ ማለት ያሉ በመኾናቸው አምላክ ሰው ለመኾኑ የትንቢት በር ከፍች ኾነዋል ይላሉ ።( የኢትዮጽያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት ገጽ-233 )
ይህን ተስፍ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላም በቤተልሔም ተወልዶ ሲገለጥ ፈጽሞለታል ። ይህን ሁሉ ዘመን ጠብቆ መወለዱ ድኅነቱን በለበሰው የሰው ስጋ የሚፈጽመው ለአዳም እና ለሔዋን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የሰው ዘር መሆኑን ያሳውቅ ዘንድ ስለወደደ ። ሰው መሆኑ በእባብ አካል ተደብቆ ወደ ውሸት የመራውን ጠላት ዲያብሎስ እራሱን በሚታይ ግዙፍ አካል ነፍስና ስጋን ነስቶ ተወልዶ ሰዎችን ሁሉ ወደ እውነት እርሱን ወደ መረዳት አንድነት ይቀላቅል ዘንድ ፈቀደ ። ኢየሱስ ክርሰቶስ ሰው ሆኖ መገለጡን ስናወራ የእኛን የሰዎችን አፈጣጠርና ጥንተ ነገር መናገር ይገባል ይለናል "ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ" ምክንያቱም ሰው ሆኖ እንዲገለጥ በእኛ መካከል እንዲገኝ ያረገው የእኛ በደል ነውና ቅዱስ ያሬድ በድጓው "ኢትዘኪሮ አበሳ ዚአነ ኢሐደገነ ፍሰሐ ኮነ ዘውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ የእኛን በደላችንን ሳያስታውስ [በኃጠአተኝነት] አልተወንም ፣ ደስታችን ሆነ ይኸው እርሱ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይለናል "[ድጓ ዘአስተምሮ] በአንቀጸ ብርሃን ደርሰቱ ደግሞ ሰማያውን መላእክት ምድራውያን የሰው ልጆች አምላክ ሰው በመሆኑ ደስተኞች መሆናቸውን "ተፈሥሑ ሰማያት" መላእክትም በመኖርያቸው "ወተሐሥየት ምድር " ደቂቀ አዳምም መኖርያቸው ። ይለናል
ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ታኀሳስ 27 2017 ዓ.ም
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ